የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘እጆቻችሁ አይዛሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መጋቢት 1
    • 11, 12. (ሀ) በቀሪዎቹ ላይ የተፈጸመው ሌላው የሶፎንያስ ትንቢት ምንድን ነው? (ለ) ቅቡዓን ቀሪዎች ‘እጆቻችሁ አይዛሉ’ የሚለውን ትእዛዝ የተከተሉት እንዴት ነው?

      11 ታማኝ የሆኑት ቅቡዓን የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት በሆነችው ታላቂቱ ባቢሎን ውስጥ ከነበሩበት መንፈሳዊ ግዞት በ1919 ነፃ ሲወጡ ተደስተዋል። ሶፎንያስ የተነበየው የሚከተለው ትንቢት በራሳቸው ላይ ሲፈጸም ተመልክተዋል፦ “የጽዮን ልጅ ሆይ፣ ዘምሪ፤ እስራኤል ሆይ፣ እልል በል፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፣ በፍጹም ልብሽ ሐሤት አድርጊ ደስም ይበልሽ። እግዚአብሔር ፍርድሽን አስወግዶአል፣ ጠላትሽንም ጥሎአል፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በመካከልሽ አለ፣ ከእንግዲህም ወዲህ ክፉ ነገርን አታዪም። በዚያን ቀን ለኢየሩሳሌም፦ ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ፣ እጆችሽም አይዛሉ። አምላክሽ እግዚአብሔር በመካከልሽ ታዳጊ ኃያል ነው . . . ይባላል።”—ሶፎንያስ 3:14-17

      12 ቅቡዓን ቀሪዎች ይሖዋ በመካከላቸው እንዳለ ጽኑ እምነት ስላላቸውና ይህንንም የሚያሳዩ ብዙ ማረጋገጫዎች ስለተመለከቱ የተሰጣቸውን መለኮታዊ ተልዕኮ በማከናወን በድፍረት ወደፊት ገፍተዋል። የመንግሥቱን ምሥራች ከመስበካቸውም በላይ ይሖዋ በሕዝበ ክርስትና፣ በተቀረው የታላቂቱ ባቢሎን ክፍልና በመላው የሰይጣን ክፉ ሥርዓት ላይ የወሰነውን ፍርድ አሳውቀዋል። ከ1919 ወዲህ ባሉት አሥርተ ዓመታት የተለያዩ ችግሮች ቢያጋጥሟቸውም “ጽዮን ሆይ፣ አትፍሪ፣ እጆችሽም አይዛሉ” የሚለውን መለኮታዊ ትእዛዝ ተከትለዋል። የይሖዋን መንግሥት የሚያውጁ በቢልዮን የሚቆጠሩ ትራክቶችን፣ መጽሔቶችን፣ መጽሐፎችንና ቡክሌቶችን በትጋት አሰራጭተዋል። ከ1935 ጀምሮ ወደ እነርሱ በመጉረፍ ከጎናቸው ለቆሙት ሌሎች በጎች እምነት የሚያጠነክሩ ምሳሌዎች ሆነዋል።

      ‘እጆቻችሁ አይዛሉ’

      13, 14. (ሀ) አንዳንድ አይሁዶች ይሖዋን ከማገልገል ወደ ኋላ ያሉት ለምንድን ነው? ይህስ የታየው እንዴት ነው? (ለ) ምን ብሎ ማሰብ ጥበብ አይሆንም? እጆቻችን መዛል የሌለባቸው በየትኛው ሥራ ነው?

      13 ታላቁን የይሖዋ ቀን ‘በጉጉት እየተጠባበቅን ባለንበት’ በአሁኑ ጊዜ ከሶፎንያስ ትንቢት ተግባራዊ እርዳታ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው? በመጀመሪያ ደረጃ የይሖዋ ቀን ቅርብ መሆኑን በመጠራጠራቸው የተነሳ ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ እንዳሉት አይሁዶች እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን። እነዚህ አይሁዶች ያደረባቸውን ጥርጣሬ አፍ አውጥተው በግልጽ አልተናገሩት ይሆናል፤ ሆኖም ታላቁ የይሖዋ ቀን ቅርብ መሆኑን ከልባቸው እንደማያምኑበት አኗኗራቸው ያሳይ ነበር። ይሖዋን በጉጉት ከመጠባበቅ ይልቅ ያተኮሩት ሀብት በማግበስበስ ላይ ነበር።—ሶፎንያስ 1:12, 13፤ 3:8

      14 ዛሬ በልባችን ውስጥ ጥርጣሬዎች እንዲተከሉ የምንፈቅድበት ጊዜ አይደለም። በአእምሯችንም ሆነ በልባችን የይሖዋ ቀን ገና ነው ብለን የምናስብ ከሆነ በጣም ሞኝነት ነው። (2 ጴጥሮስ 3:1-4, 10) ይሖዋን ከመከተል ወደ ኋላ ማለት ወይም በይሖዋ አገልግሎት ‘እጆቻችን እንዲዝሉ መፍቀድ’ የለብንም። ይህም ‘ምሥራቹን’ በመስበኩ ሥራ ‘ያለመታከት’ መካ­ፈልን ያካትታል።—ምሳሌ 10:4፤ ማርቆስ 13:10

  • ‘እጆቻችሁ አይዛሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መጋቢት 1
    • 16. አብዛኞቹ የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት አባላት ምን አስተሳሰብ አላቸው? ሆኖም ይሖዋ ምን ማበረታቻ ይሰጠናል?

      16 በዛሬው ጊዜ ግድ የለሽነት በብዙ የምድር ክፍሎች በተለይም በበለጸጉት አገሮች ውስጥ በእጅጉ ተስፋፍቷል። ሌላው ቀርቶ የሕዝበ ክርስትና አብያተ ክርስቲያናት አባላት እንኳ ይሖዋ አምላክ በአሁኑ ጊዜ በሰዎች ጉዳይ እጁን ያስገባል ብለው አያምኑም። እነዚህ ሰዎች በማፌዝ ወይም “አልፈልግም” የሚል አጭር መልስ በመስጠት የመንግሥቱን ምሥራች ለማድረስ የምናደርገውን ጥረት መና ለማስቀረት ይሞክራሉ። እነዚህ ሁኔታዎች እያሉ በምስክርነቱ ሥራ መጽናት ተፈታታኝ ሊሆን ይችላል። ያለንን ጽናት ይፈትነዋል። ሆኖም ይሖዋ በሶፎንያስ ትንቢት አማካኝነት እንደሚከተለው በማለት ታማኝ ሕዝቦቹን ያበረታታል፦ “እጆችሽም አይዛሉ። አምላክሽ ይሖዋ በመካከልሽ ነው። እርሱ ኃያል እንደመሆኑ መጠን ይታደጋል። በደስታ በአንቺ ደስ ይለዋል፣ በፍቅሩም ያርፋል፣ በእልልታም በአንቺ ደስ ይለዋል።”—ሶፎንያስ 3:16, 17 አዓት

      17. አዳዲስ የሆኑ የሌሎች በጎች አባላት ሊከተሉት የሚገባቸው ግሩም ምሳሌ ምንድን ነው? እንዴትስ?

      17 ዘመናዊው የይሖዋ ሕዝቦች ታሪክ እንደሚያሳየው ቅቡዓኑና ረጅም ዕድሜ ያሳለፉ የሌሎች በጎች አባላት በእነዚህ የመጨረሻ ቀኖች ውስጥ አስደናቂ የመሰብሰብ ሥራ አከናውነዋል። እነዚህ ታማኝ ክርስቲያኖች ለአያሌ አሥርተ ዓመታት ጸንተዋል። በሕዝበ ክርስትና ሥር ያሉ አብዛኞቹ ሰዎች የሚያሳዩአቸው ግድ የለሽነት ተስፋ እንዲያስቆርጣቸው አልፈቀዱም። ከሌሎች በጎች መካከል የሆኑ አዳዲስ ሰዎችም ቢሆኑ በዛሬው ጊዜ በብዙ አገሮች በተስፋፋው ሰዎች ለመንፈሳዊ ነገሮች በሚያሳዩት ግድ የለሽነት ተስፋ መቁረጥ የለባቸውም። ‘እጆቻቸው ሊዝሉ’ ወይም ሊታክቱ አይገባም። መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እንዲሁም በግ መሰል ሰዎችን ስለ ይሖዋ ቀንና ከዚያ በኋላ ስለሚመጡ በረከቶች እውነተኛውን እውቀት እንዲያገኙ ለመርዳት የተዘጋጁ ሌሎች ጽሑፎችን ለማበርከት እያንዳንዱን አጋጣሚ መጠቀም ይገባቸዋል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ