-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
6-8. ሶፎንያስ 1:4-6 ላይ በትንቢት የተነገረው ምንድን ነው? ትንቢቱስ በጥንቷ ይሁዳ ላይ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነበር?
6 ሶፎንያስ 1:4-6 አምላክ በሐሰተኛ አምላኪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ሲተነብይ እንዲህ ይላል:- “እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፤ በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፣ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፣ እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፣ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።”
-
-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
9. (ሀ) ሕዝበ ክርስትና ጥፋተኛ የሆነችው በምን ረገድ ነው? (ለ) በይሁዳ ከነበሩት እምነት አጉዳዮች በተለየ መልኩ ምን ለማድረግ መወሰን ይኖርብናል?
9 ይህ ሁሉ በሐሰት አምልኮና በኮከብ ቆጠራ የተዘፈቀችውን ሕዝበ ክርስትና ያስታውሰናል። በቀሳውስት ደጋፊነት በተካሄዱ ውጊያዎች መሠውያ ላይ በሚልዮን የሚቆጠር ሕይወት ለመሥዋዕት በማቅረብ ረገድ የተጫወተችው ሚና በእርግጥም የሚዘገንን ነው! ‘ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ ተመልሰው’ ግድ የለሾች የሆኑትንና ይሖዋንና መመሪያውን መፈለግ ያቆሙትን የይሁዳን ከዳተኞች ከመምሰል እንራቅ። ከዚህ ይልቅ ለአምላክ ያለንን ፍጹም አቋም እንጠብቅ።
-