-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
17. በሶፎንያስ 1:14-16 መሠረት የይሖዋ የፍርድ ቀን ምን ያህል ቅርብ ነው?
17 የይሖዋ የፍርድ ቀን ምን ያህል ቀርቧል? በሶፎንያስ 1:14-16 መሠረት አምላክ የሚከተለውን ዋስትና ይሰጣል:- “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፤ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል። ያ ቀን የመዓት ቀን፣ የመከራና የጭንቀት ቀን፣ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፣ በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።”
-
-
የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
-
-
19, 20. (ሀ) የአምላክ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የተፈጸመባቸው አንዳንድ ገጽታዎች ምንድን ነበሩ? (ለ) ይህ የነገሮች ሥርዓት ከሚጠብቀው ጥፋት አንጻር ሲታይ ምን ጥያቄዎች ይነሳሉ?
19 የአምላክ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ በተገለጠበት ጊዜ “የመከራና የጭንቀት ቀን” ሆኖባቸው ነበር። የይሁዳ ነዋሪዎች ከፊታቸው የተደቀነው ሞትና ጥፋት ከሚያስከትልባቸው የአእምሮ ጭንቀት በተጨማሪ ባቢሎናውያኑ ወራሪዎች ብዙ መከራ አድርሰውባቸዋል። ያ ወቅት በጭስና በእልቂት የተሞላ ስለሆነ በምሳሌያዊ አነጋገር ብቻ ሳይሆን ምናልባትም ቃል በቃል “የጨለማና የጭጋግ ቀን” ሆኗል። “የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን” ቢሆንም ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ምንም ፋይዳ አልነበረውም።
-