የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
    • 17. በሶፎንያስ 1:​14-16 መሠረት የይሖዋ የፍርድ ቀን ምን ያህል ቅርብ ነው?

      17 የይሖዋ የፍርድ ቀን ምን ያህል ቀርቧል? በሶፎንያስ 1:​14-16 መሠረት አምላክ የሚከተለውን ዋስትና ይሰጣል:- “ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቀን ድምፅ ቀርቦአል እጅግም ፈጥኖአል፤ ኃያሉም በዚያ በመራራ ልቅሶ ይጮኻል። ያ ቀን የመዓት ቀን፣ የመከራና የጭንቀት ቀን፣ የመፍረስና የመጥፋት ቀን፣ የጨለማና የጭጋግ ቀን፣ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን፣ በተመሸጉ ከተሞችና በረዘሙ ግንቦች ላይ የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን ነው።”

  • የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
    • 19, 20. (ሀ) የአምላክ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ የተፈጸመባቸው አንዳንድ ገጽታዎች ምንድን ነበሩ? (ለ) ይህ የነገሮች ሥርዓት ከሚጠብቀው ጥፋት አንጻር ሲታይ ምን ጥያቄዎች ይነሳሉ?

      19 የአምላክ ቁጣ በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ በተገለጠበት ጊዜ “የመከራና የጭንቀት ቀን” ሆኖባቸው ነበር። የይሁዳ ነዋሪዎች ከፊታቸው የተደቀነው ሞትና ጥፋት ከሚያስከትልባቸው የአእምሮ ጭንቀት በተጨማሪ ባቢሎናውያኑ ወራሪዎች ብዙ መከራ አድርሰውባቸዋል። ያ ወቅት በጭስና በእልቂት የተሞላ ስለሆነ በምሳሌያዊ አነጋገር ብቻ ሳይሆን ምናልባትም ቃል በቃል “የጨለማና የጭጋግ ቀን” ሆኗል። “የመለከትና የሰልፍ ጩኸት ቀን” ቢሆንም ማስጠንቀቂያ መሰጠቱ ምንም ፋይዳ አልነበረውም።

      20 ባቢሎናውያን ‘ረዥም ግንቦችን’ ሲደረማምሱ በጥበቃ ላይ የነበሩ የኢየሩሳሌም ጉበኞች የሚደርስላቸው አጥተዋል። በዘመናችንም የዚህ ክፉ የነገሮች ሥርዓት ምሽጎች ዒላማቸውን ብቻ መርጠው የሚያወድሙትን የአምላክ ሰማያዊ ጦር መሣሪያዎች መመከት የማይችሉ ይሆናሉ። ከጥፋቱ ለመትረፍ ተስፋ ታደርጋለህን? ‘የሚወድዱትን ሁሉ ከሚጠብቀው፣ ኃጢአተኞችንም ሁሉ ከሚያጠፋው’ ከይሖዋ ጎን በመሆን ጽኑ አቋም ይዘሃልን?​—⁠መዝሙር 145:​20

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ