የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በጉጉት እየተጠባበቃችሁኝ ኑሩ”
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መጋቢት 1
    • 13. ሶፎንያስ በሞዓብ፣ በአሞንና በአሦር ላይ የተናገረው የፍርድ መልእክት ምንድን ነው?

      13 በተጨማሪም ይሖዋ ሕዝቡን ባሠቃዩት ብሔራት ላይ ያለውን ቁጣ በነቢዩ ሶፎንያስ አማካኝነት ተናግሯል። እንዲህ ብሏል፦ “በሕዝቤም ላይ ያላገጡባትን፣ በድንበራቸውም ላይ እየታበዩ የተናገሩባትን የሞዓብን ማላገጥና የአሞንን ልጆች ስድብ ሰምቻለሁ። ስለዚህ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና በእርግጥ ሞዓብ እንደ ሰዶም፣ የአሞንም ልጆች እንደ ገሞራ፣ የሳማ ስፍራና የጨው ጉድጓድ ለዘላለምም ምድረ በዳ ሆነው ይኖራሉ፤ . . . እርሱም በሰሜን ላይ እጁን ይዘረጋል፣ አሦርንም ያጠፋል፤ ነነዌንም ባድማ፣ እንደ በረሃም ደረቅ ያደርጋታል።”—ሶፎንያስ 2:8, 9, 13

      14. የውጪ ብሔራት በእስራኤላውያንና በአምላካቸው በይሖዋ ላይ ‘እንደታበዩ’ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?

      14 ሞዓብና አሞን የእስራኤላውያን የረጅም ጊዜ ጠላቶች ነበሩ። (ከመሳፍንት 3:12-14 ጋር አወዳድር።) ፓሪስ ውስጥ በሉቭር ሙዚየም በሚገኘው የሞዓባውያን ጽላት ላይ የተቀረጸው ጽሑፍ የሞዓባውያን ንጉሥ የነበረው ሞሳ የተናገራቸውን የጉራ ቃላት ይዟል። ካሞሽ በተባለው አምላኩ እርዳታ ብዙ የእስራኤል ከተሞችን እንደያዘ በኩራት ይተርካል። (2 ነገሥት 1:1) አሞናውያን ሚልኮም በተባለው አምላካቸው ስም ጋድ ተብሎ የሚጠራውን የእስራኤል ክልል እንደያዙ በሶፎንያስ ዘመን ይኖር የነበረው ኤርምያስ ተናግሯል። (ኤርምያስ 49:1) በተጨማሪም የአሦራውያን ንጉሥ ስልምናሶር አምስተኛ ሶፎንያስ ከኖረበት ዘመን አንድ መቶ ዓመት ቀደም ብሎ ሰማርያን በመውረር በቁጥጥሩ ሥር አውሏት ነበር። (2 ነገሥት 17:1-6) ከጥቂት ጊዜ በኋላ ንጉሥ ሰናክሬም በይሁዳ ላይ ጥቃት በመሰንዘር በይሁዳ የሚገኙ አያሌ የተመሸጉ ከተሞች በቁጥጥሩ ሥር አድርጎ ነበር። አልፎ ተርፎም ኢየሩሳሌምን እንደሚወጋ ዝቶ ነበር። (ኢሳይያስ 36:1, 2) የአሦር ንጉሥ ቃል አቀባይ ኢየሩሳሌምን አሳልፈው እንዲሰጡ ሲጠይቅ በይሖዋ ላይ የትዕቢት ቃል ተናግሮ ነበር።—ኢሳይያስ 36:4-20

  • “በጉጉት እየተጠባበቃችሁኝ ኑሩ”
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መጋቢት 1
    • 15. ይሖዋ በሕዝቦቹ ላይ የታበዩ ብሔራት የሚያመልኳቸውን አማልክት ያዋረደው እንዴት ነበር?

      15 መዝሙር 83 “ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፣ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ” ብለው ጉራቸውን በመንዛት በእስራኤል ላይ የታበዩ እንደ ሞዓብ፣ አሞንና አሦር ያሉ ብዙ ብሔራት ይጠቅሳል። (መዝሙር 83:4) የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እነዚህን ሁሉ ትዕቢተኛ ብሔራትና አማልክቶቻቸውን እንደሚያዋርድ ነቢዩ ሶፎንያስ በድፍረት አስታውቋል። “በሠራዊት ጌታ በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ አላግጠዋልና፣ እየታበዩም ተናግረዋልና ይህ ስለ ትዕቢታቸው ያገኛቸዋል። እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፣ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፤ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።”—ሶፎንያስ 2:10, 11

  • “በጉጉት እየተጠባበቃችሁኝ ኑሩ”
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | መጋቢት 1
    • 17. የሶፎንያስ የፍርድ መልእክት በብሔራት ላይ መፈጸም የጀመረው መቼና እንዴት ነው?

      17 ይህንን ማስጠንቀቂያ የሰሙ ሰዎች በተፈጠረው ሁኔታ አልተደናገጡም ነበር። ብዙዎቹ በሕይወት ቆይተው የሶፎንያስ ትንቢት ሲፈጸም አይተዋል። ባቢሎናውያን፣ ሜዶናውያን እና ሲዚያንስ ይሆናሉ ተብለው የሚገመቱት ከሰሜን የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ኅብረት በመፍጠር በ632 ከዘአበ ነነዌን ወርረው አጥፍተዋት ነበር። ታሪክ ጸሐፊው ዊል ዱራንት እንዲህ ብለዋል፦ “በናቦፖላሳር የሚመራው የባቢሎናውያን ሠራዊት በሲያክስሬዝ ከሚመራው የሜዶናውያን ሠራዊትና በኮከሶስ ከሚኖሩት የሲዚያንስ ሠራዊት ጋር በመተባበር በሚያስደንቅ ፍጥነትና ያለምንም ችግር የከተማይቱን የሰሜን ቅጥር ተቆጣጠረ። . . . አሦር በአንድ ጊዜ ከታሪክ ማኅደር ተሰረዘች።” ሶፎንያስ ይህ እንደሚሆን በትክክል ተንብዮ ነበር።—ሶፎንያስ 2:13-15

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ