የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
    • 6-8. ሶፎንያስ 1:​4-6 ላይ በትንቢት የተነገረው ምንድን ነው? ትንቢቱስ በጥንቷ ይሁዳ ላይ ፍጻሜውን ያገኘው እንዴት ነበር?

      6 ሶፎንያስ 1:​4-6 አምላክ በሐሰተኛ አምላኪዎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ ሲተነብይ እንዲህ ይላል:- “እጄንም በይሁዳ ላይ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ሁሉ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከዚህም ስፍራ የበኣልን ቅሬታና የጣዖታቱን ካህናት ስም አጠፋለሁ፤ በሰገነትም ላይ ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን፣ በእግዚአብሔርና በንጉሣቸው በሚልኮም ምለው የሚሰግዱትን፣ እግዚአብሔርንም ከመከተል የተመለሱትን፣ እግዚአብሔርንም ያልፈለጉትንና ያልጠየቁትን አጠፋለሁ።”

  • የይሖዋ የፍርድ ቀን ቀርቧል!
    መጠበቂያ ግንብ—2001 | የካቲት 15
    • 8 በተጨማሪም አምላክ በከዋክብት ቆጠራ ድርጊቶች በመካፈልና ፀሐይን በማምለክ ‘ለሰማይ ሠራዊት የሚሰግዱትን’ ይቆርጣል። (2 ነገሥት 23:​11፤ ኤርምያስ 19:​13፤ 32:​29) ከዚህም በላይ ‘በይሖዋና በሚልኮም እየማሉ’ እውነተኛውን አምልኮ ከሐሰተኛው ጋር ለመቀላቀል የሚሞክሩትን ሁሉ ያጠፋል። ሚልኮም የአሞናውያን ዋነኛ አምላክ የሆነው የሞሎክ ሌላ መጠሪያ ሊሆን ይችላል። የሞሎክ አምልኮ ሕፃናትን መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብን ይጨምር ነበር።​—⁠1 ነገሥት 11:​5፤ ኤርምያስ 32:​35

      የሕዝበ ክርስትና ፍጻሜ ቀርቧል!

      9. (ሀ) ሕዝበ ክርስትና ጥፋተኛ የሆነችው በምን ረገድ ነው? (ለ) በይሁዳ ከነበሩት እምነት አጉዳዮች በተለየ መልኩ ምን ለማድረግ መወሰን ይኖርብናል?

      9 ይህ ሁሉ በሐሰት አምልኮና በኮከብ ቆጠራ የተዘፈቀችውን ሕዝበ ክርስትና ያስታውሰናል። በቀሳውስት ደጋፊነት በተካሄዱ ውጊያዎች መሠውያ ላይ በሚልዮን የሚቆጠር ሕይወት ለመሥዋዕት በማቅረብ ረገድ የተጫወተችው ሚና በእርግጥም የሚዘገንን ነው! ‘ይሖዋን ከመከተል ወደኋላ ተመልሰው’ ግድ የለሾች የሆኑትንና ይሖዋንና መመሪያውን መፈለግ ያቆሙትን የይሁዳን ከዳተኞች ከመምሰል እንራቅ። ከዚህ ይልቅ ለአምላክ ያለንን ፍጹም አቋም እንጠብቅ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ