-
የናሆም፣ የዕንባቆምና የሶፎንያስ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ኅዳር 15
-
-
3:9 የ1954 ትርጉም—‘ንጹሕ ልሳን’ ምንድን ነው? የሚነገረውስ እንዴት ነው? ንጹሕ ልሳን የአምላክ ቃል በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው የአምላክ እውነት ነው። ይህ ልሳን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን በሙሉ ያጠቃልላል። እውነትን በማመን፣ እውነትን ለሌሎች በትክክል በማስተማርና ከአምላክ ፈቃድ ጋር ተስማምተን በመኖር ይህን ልሳን መናገር እንችላለን።
-
-
የናሆም፣ የዕንባቆምና የሶፎንያስ መጻሕፍት ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ኅዳር 15
-
-
3:8, 9 [የ1954 ትርጉም]፦ የይሖዋን ቀን በምንጠባበቅበት በዚህ ወቅት ‘ንጹሑን ልሳን’ በመማርና ራሳችንን ለይሖዋ ወስነን ‘ስሙን በመጥራት’ ከቁጣው ለመዳን መዘጋጀት እንችላለን። ከዚህም በተጨማሪ ከይሖዋ ሕዝቦች ጋር ‘ተስማምተን’ እሱን እናገለግላለን እንዲሁም “የምስጋናን መሥዋዕት” እናቀርብለታለን።—ዕብራውያን 13:15
-