-
እውነተኛ አምልኮ ሰዎችን አንድ ያደርጋልመጠበቂያ ግንብ—2001 | መስከረም 15
-
-
በጊዜያችን የታየ ዓለም አቀፍ አንድነት!
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው የሶፎንያስ መጽሐፍ ውስጥ የሚገኝ አንድ አስደናቂ ትንቢት የተለያየ ባህልና አስተዳደግ ያላቸው ሰዎች በአንድነት ስለሚሰባሰቡበት ጊዜ ይናገራል። እንዲህ ይላል:- “በዚያን ጊዜም አሕዛብ ሁሉ አንድ ሆነው እግዚአብሔርን ያገለግሉት ዘንድ ስሙን እንዲጠሩ ንጹሕን ልሳን እመልስላቸዋለሁ።” (ሶፎንያስ 3:9) ይህ ተለውጠው አምላክን በአንድነት የሚያገለግሉትን ሰዎች የሚያመለክት እንዴት ያለ ግሩም መግለጫ ነው!
-
-
እውነተኛ አምልኮ ሰዎችን አንድ ያደርጋልመጠበቂያ ግንብ—2001 | መስከረም 15
-
-
ይሖዋ ሕዝቡን አንድ ለማድረግ ንጹሕ ልሳን ይሰጣቸዋል። ይህ አዲስ ልሳን ስለ አምላክና ስለ ዓላማዎቹ የሚገልጸውን የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት በትክክል ማስተዋልን ይጨምራል። ንጹሑን ልሳን መናገር ማለት ደግሞ በእውነት ማመንን፣ ይህንን እውነት ለሌሎች ማስተማርንና ከአምላክ ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር ተስማምቶ መኖርን ያካትታል። ይህም ከፋፋይ ከሆነው ፖለቲካ መራቅንና የዚህ ዓለም መለያ ምልክት የሆኑትን እንደ ዘረኝነትና ብሔረተኝነት ያሉትን ከራስ ወዳድነት የሚመነጩ ባሕርያት ከልብ ነቅሎ ማውጣትን ይጠይቃል። (ዮሐንስ 17:14፤ ሥራ 10:34, 35) እውነትን የሚወዱ ቅን ልብ ያላቸው ሰዎች ሁሉ ይህንን ልሳን መማር ይችላሉ። ቀደም ባለው ርዕስ ላይ የተጠቀሱት አምስት ግለሰቦች በአንድ ወቅት ፈጽሞ የተለያየ ሃይማኖታዊ እምነት የነበራቸው ቢሆንም እውነተኛ ለሆነው አምላክ ለይሖዋ ብቻ በሚቀርበው አምልኮ እንዴት አንድ እንደሆኑ ተመልከት።
-