የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 38—ዘካርያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 6 አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተቺዎች ከምዕራፍ 9 በኋላ የመጽሐፉ አጻጻፍ ስልት መቀየሩ ይኸኛውን ክፍል የጻፈው ዘካርያስ አለመሆኑን እንደሚጠቁም ይናገራሉ። ይሁን እንጂ የአጻጻፉ ስልት የተለወጠው መልእክቱም በመለወጡ ነው። የመጀመሪያዎቹ ስምንት ምዕራፎች ያተኮሩት በዘካርያስ ዘመን የነበሩት ሰዎች በወቅቱ በሚያስፈልጓቸው ነገሮች ላይ ሲሆን ከ9 እስከ 14 ባሉት ምዕራፎች ውስጥ ደግሞ ነቢዩ ወደፊት ስለሚፈጸሙ ነገሮች ጽፏል። ማቴዎስ፣ ዘካርያስ የጻፋቸውን ቃላት ጠቅሶ ኤርምያስ እንደተናገራቸው አድርጎ የጻፈበትን ምክንያት በተመለከተ አንዳንዶች ጥያቄ አንስተዋል። (ማቴ. 27:9፤ ዘካ. 11:12) የኋለኞቹ ነቢያት የሚባሉት መጻሕፍት አሁን ባለን መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሚገኘው በኢሳይያስ ሳይሆን በኤርምያስ የሚጀምሩበት ወቅት የነበረ ይመስላል፤ በመሆኑም ማቴዎስ ዘካርያስን ሲጠቅስ “ኤርምያስ” ብሎ የተናገረው፣ በአይሁዳውያን ዘንድ የሚሠራበትን በአንድ ክፍል ውስጥ ያሉትን ቅዱሳን ጽሑፎች በአጠቃላይ በመጀመሪያው መጽሐፍ ስም የመጥራት ልማድ ተከትሎ ሊሆን ይችላል። ኢየሱስ ራሱ መጻሕፍት በመባል የሚታወቁትን ክፍሎች ሁሉ አጠቃልሎ ሲናገር “በመዝሙር መጻሕፍት” ብሏል።—ሉቃስ 24:44b

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 38—ዘካርያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 25 ቀደም ባሉት አንቀጾች ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ “ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ” ንጉሥ በመሆን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚገባ፣ ‘በሠላሳ ብር’ አልፎ እንደሚሰጥ፣ በሚያዝበት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ እንደሚበተኑና ተሰቅሎ እያለ ወታደሮቹ በጦር እንደሚወጉት በዘካርያስ መጽሐፍ ውስጥ በትክክል ትንቢት ተነግሮ ነበር። (ዘካ. 9:9፤ 11:12፤ 13:7፤ 12:10) በተጨማሪም ትንቢቱ የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚሠራውን ግለሰብ “ቅርንጫፍ” ብሎ ይጠራዋል። ኢሳይያስ 11:1-10ን፣ ኤርምያስ 23:5ን እና ሉቃስ 1:32, 33ን ስናወዳድር ይህ ቅርንጫፍ “በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል” የተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንረዳለን። ዘካርያስ ይህን “ቅርንጫፍ” በተመለከተ “በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል” በማለት የተናገረ ሲሆን ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ “ኢየሱስ . . . እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኖአል” እንዲሁም ‘በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል’ በማለት ከጻፈው ሐሳብ ጋር ይስማማል። (ዘካ. 6:12, 13፤ ዕብ. 6:20፤ 8:1) በመሆኑም ትንቢቱ “ቅርንጫፍ” የተባለው በሰማያት በአምላክ ቀኝ ሊቀ ካህናትና ንጉሥ መሆኑን እንዲሁም ይሖዋ ከሁሉ በላይ ሉዓላዊ ገዥ መሆኑን እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] አንድ፣ ስሙም አንድ ብቻ ይሆናል።”—ዘካ. 14:9

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ