የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 38—ዘካርያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 5 መጽሐፉ በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት እንደተጻፈ የሚያሳየው ከሁሉ የበለጠው አሳማኝ ማስረጃ ግን መሲሑን፣ ክርስቶስ ኢየሱስን በሚመለከት የተነገሩት ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ማግኘታቸው ሲሆን የሚከተሉትን ጥቅሶች በማወዳደር ይህን ማየት ይቻላል:- ዘካርያስ 9:9ን ከማቴዎስ 21:4, 5 እና ከዮሐንስ 12:14-16፤ ዘካርያስ 12:10ን ከዮሐንስ 19:34-37፤ እንዲሁም ዘካርያስ 13:7ን ከማቴዎስ 26:31 እና ከማርቆስ 14:27 ጋር አወዳድር። በተጨማሪም በዘካርያስ 8:16 እና ኤፌሶን 4:25፤ በዘካርያስ 3:2 እና ይሁዳ 9 እንዲሁም በዘካርያስ 14:5 እና ይሁዳ 14 መካከል ያሉትን ተመሳሳይነቶች ልብ ማለት ይገባል። በእርግጥም በአምላክ ቃል ውስጥ የሚታየው ስምምነት በጣም የሚያስደንቅ ነው!

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 38—ዘካርያስ
    “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 15
    • 25 ቀደም ባሉት አንቀጾች ላይ እንደተገለጸው ኢየሱስ “ትሑት ሆኖ፣ በአህያ ላይ ተቀምጦ” ንጉሥ በመሆን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚገባ፣ ‘በሠላሳ ብር’ አልፎ እንደሚሰጥ፣ በሚያዝበት ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ እንደሚበተኑና ተሰቅሎ እያለ ወታደሮቹ በጦር እንደሚወጉት በዘካርያስ መጽሐፍ ውስጥ በትክክል ትንቢት ተነግሮ ነበር። (ዘካ. 9:9፤ 11:12፤ 13:7፤ 12:10) በተጨማሪም ትንቢቱ የይሖዋን ቤተ መቅደስ የሚሠራውን ግለሰብ “ቅርንጫፍ” ብሎ ይጠራዋል። ኢሳይያስ 11:1-10ን፣ ኤርምያስ 23:5ን እና ሉቃስ 1:32, 33ን ስናወዳድር ይህ ቅርንጫፍ “በያዕቆብም ቤት ላይ ለዘላለም ይነግሣል” የተባለለት ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሆነ እንረዳለን። ዘካርያስ ይህን “ቅርንጫፍ” በተመለከተ “በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል” በማለት የተናገረ ሲሆን ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ “ኢየሱስ . . . እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ሊቀ ካህናት ሆኖአል” እንዲሁም ‘በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል’ በማለት ከጻፈው ሐሳብ ጋር ይስማማል። (ዘካ. 6:12, 13፤ ዕብ. 6:20፤ 8:1) በመሆኑም ትንቢቱ “ቅርንጫፍ” የተባለው በሰማያት በአምላክ ቀኝ ሊቀ ካህናትና ንጉሥ መሆኑን እንዲሁም ይሖዋ ከሁሉ በላይ ሉዓላዊ ገዥ መሆኑን እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW] አንድ፣ ስሙም አንድ ብቻ ይሆናል።”—ዘካ. 14:9

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ