-
ጥበቃ ከምታገኙበት ከይሖዋ ሸለቆ አትውጡመጠበቂያ ግንብ—2013 | የካቲት 15
-
-
8. (ሀ) ተራሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ያመለክታሉ? (ለ) ‘የደብረ ዘይት ተራራ’ ምን ያመለክታል?
8 “ከተማዪቱ” ማለትም ኢየሩሳሌም የምታመለክተው ሰማያዊቷን ኢየሩሳሌም እንደሆነ ሁሉ “ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ” የሚገኘው “የደብረ ዘይት ተራራም” ምሳሌያዊ ሊሆን ይገባል። ይህ ተራራ ምን ያመለክታል? ተራራው ‘ለሁለት ተከፍሎ’ ሁለት ተራሮች የሚሆነው እንዴት ነው? ይሖዋ እነዚህን ተራሮች “ተራሮቼ” (NW) ያላቸው ለምንድን ነው? (ዘካርያስ 14:3-5ን አንብብ።) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተራሮች አገዛዝን ወይም መንግሥታትን ለማመልከት ተሠርቶባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የአምላክ ተራራ በረከት እንዲሁም ደህንነት እንደሚገኝበት ቦታ ተደርጎ ተገልጿል። (መዝ. 72:3፤ ኢሳ. 25:6, 7) ከዚህ አንጻር፣ ከምድራዊቷ ኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ የሚገኘው አምላክ የቆመበት የደብረ ዘይት ተራራ የይሖዋን አጽናፈ ዓለማዊ ሉዓላዊነት ወይም የበላይ ገዥነቱን ያመለክታል።
-
-
ጥበቃ ከምታገኙበት ከይሖዋ ሸለቆ አትውጡመጠበቂያ ግንብ—2013 | የካቲት 15
-
-
ወደ ሸለቆው መሸሽ ተጀመረ!
11, 12. (ሀ) ወደ ምሳሌያዊው ሸለቆ መሸሽ የተጀመረው መቼ ነው? (ለ) ይሖዋ በኃያል ክንዱ ሕዝቡን እንደሚያድን የሚያረጋግጥልን ምንድን ነው?
11 ኢየሱስ “በስሜ ምክንያት በሕዝቦች ሁሉ ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” በማለት ተከታዮቹን አስጠንቅቋቸው ነበር። (ማቴ. 24:9) ከ1914 ወዲህ ይኸውም በዚህ ሥርዓት የመጨረሻ ቀናት ደግሞ ይህ ጥላቻ ይበልጥ እየከረረ መጥቷል። ቅቡዓን ቀሪዎች በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በጠላቶቻቸው ከፍተኛ ጥቃት ቢሰነዘርባቸውም ጨርሶ አልጠፉም። የዓለም የሐሰት ሃይማኖቶችን ከምትወክለው ከታላቂቱ ባቢሎን መዳፍ በ1919 ነፃ ወጥተዋል። (ራእይ 11:11, 12)a የአምላክ ሕዝቦች በይሖዋ ተራሮች መካከል ወዳለው ሸለቆ መሸሽ የጀመሩት በዚህ ወቅት ነው።
12 ከ1919 አንስቶ በምድር ዙሪያ የሚገኙ የይሖዋ እውነተኛ አምላኪዎች በሸለቆው ውስጥ መለኮታዊ ጥበቃ እያገኙ ነው። ባለፉት አሥርተ ዓመታት ውስጥ በዓለም ዙሪያ በርካታ አገሮች የይሖዋ ምሥክሮች በሚያካሂዱት የስብከት እንቅስቃሴና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎቻቸው ላይ እገዳ ጥለዋል። የይሖዋ ምሥክሮች በአንዳንድ አገሮች ውስጥ አሁንም በእገዳ ሥር ናቸው። ይሁንና ብሔራት የቱንም ያህል ጥረት ቢያደርጉ እውነተኛውን አምልኮ ከምድር ገጽ ማጥፋት አይችሉም! ይሖዋ በኃያል ክንዱ ሕዝቡን ያድናል።—ዘዳ. 11:2
13. የይሖዋን ጥበቃ ከምናገኝበት ሸለቆ ሳንወጣ መኖር የምንችለው እንዴት ነው? ይህን ማድረጋችን በዛሬው ጊዜ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?
13 ከይሖዋ ጋር ተጣብቀን ከቀጠልንና በእውነት ውስጥ ጸንተን ከቆምን ይሖዋ እና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ጥበቃ ያደርጉልናል፤ አምላክ ማንኛውም አካል ወይም ምንም ነገር ‘ከእጁ እንዲነጥቀን’ አይፈቅድም። (ዮሐ. 10:28, 29) ይሖዋ የአጽናፈ ዓለሙ ሉዓላዊ ገዥ መሆኑን ተቀብለን እሱን ለመታዘዝ እንዲሁም ለመሲሐዊው መንግሥት በታማኝነት ለመገዛት ጥረት ስናደርግ የሚያስፈልገንን ማንኛውም እርዳታ ለመስጠት አምላክ ፈቃደኛ ነው። እየቀረበ ባለው ታላቁ መከራ ወቅት የይሖዋ እውነተኛ አምላኪዎች በዚህ ሸለቆ ውስጥ መሆናቸው ይበልጥ አስፈላጊ ስለሚሆን በአሁኑ ጊዜ ከሸለቆው ሳንወጣ መኖራችን የግድ ነው።
-