የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁለቱን ምሥክሮች እንደገና ሕያው ማድረግ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • 14. (ሀ) ዘካርያስ በራእይ የተመለከታቸው ሁለት የወይራ ዛፎች የምን ምሳሌዎች ነበሩ? መቅረዙስ? (ለ) በአንደኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በቅቡዓን ክርስቲያኖች ላይ ምን ደርሶባቸዋል?

      14 ዘካርያስ ይኖር የነበረበት ዘመን የእድሳትና የግንባታ ዘመን ነበር። የሁለቱን የወይራ ዛፎች ራእይ መመልከቱ ደግሞ ዘሩባቤልና ኢያሱ ሕዝቦቻቸውን ለሥራ በሚያነሳሱበት ጊዜ የይሖዋ መንፈስ አብሮአቸው እንደሚሆን የሚያመልክት ነው። ዘካርያስ በራእይ የተመለከተው የመቅረዝ ራእይ “የጥቂቱን ነገር ቀን” እንዳይንቅ የሚያሳስበው ነበር። ምክንያቱም የይሖዋ ዓላማ የሚፈጸመው “በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር [“ይሖዋ፣” NW]።” (ዘካርያስ 4:6, 10፤ 8:9) በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ለሰው ልጆች የእውነትን ብርሃን በትጋት ያደርሱ የነበሩት ጥቂት ክርስቲያኖችም በተመሳሳይ የግንባታ ሥራ ይፈጽማሉ። እነርሱም ለሌሎች የመጽናናት ምንጭ ይሆናሉ። ቁጥራቸው ጥቂት ቢሆንም “የጥቂቱን ነገር ቀን” ሳይንቁ በይሖዋ ኃይል መመካትን ይማራሉ።

  • ሁለቱን ምሥክሮች እንደገና ሕያው ማድረግ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
    • [በገጽ 165 ላይ የሚገኙ ሥዕሎች]

      ዘሩባቤልና ኢያሱ ያከናወኑት የግንባታ ሥራ በጌታ ቀን የይሖዋ ምሥክሮች ከአነስተኛ ሁኔታ ተነስተው ትልቅ ጭማሪ እንደሚያገኙ ያመለክታል። እያደገ የሄደውን ፍላጎት ለማሟላት ሲባል በብሩክሊን ኒው ዮርክ የሚገኙትን ከላይ የሚታዩትን የመሳሰሉ ሕንጻዎች ማስፋት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ