የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘካርያስ ካያቸው ራእዮች ምን ትምህርት እናገኛለን?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ጥቅምት
    • 16. (ሀ) በመቀጠል ዘካርያስ የኢፍ መስፈሪያው ምን ሲሆን ተመለከተ? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል 3 ተመልከት።) (ለ) ክንፍ ያላቸው ሁለት ሴቶች የኢፍ መስፈሪያውን ወዴት ወሰዱት?

      16 በመቀጠልም ዘካርያስ የራዛ ዓይነት ጠንካራ ክንፎች ያሏቸው ሁለት ሴቶች ተመለከተ። (ዘካርያስ 5:9-11⁠ን አንብብ።) እነዚህ ሴቶች በመስፈሪያው ውስጥ ካለችው ሴት ፈጽሞ የተለዩ ነበሩ! በጠንካራ ክንፎቻቸው ተወንጭፈው በመምጣት “ክፋትን” የያዘውን መስፈሪያ ወደ ላይ አነሱት። መስፈሪያውን ወዴት ይወስዱት ይሆን? መስፈሪያውን ወስደው ‘በሰናኦር ምድር’ ማለትም በባቢሎን አስቀመጡት። ለመሆኑ እነዚህ ሴቶች መስፈሪያውን ወደ ባቢሎን የወሰዱት ለምንድን ነው?

      17, 18. (ሀ) ሰናኦር “ክፋትን” ለማስቀመጥ ‘ተገቢ ቦታ’ ነው የምንለው ለምንድን ነው? (ለ) ክፋትን በተመለከተ ቁርጥ ውሳኔያችን ምን መሆን አለበት?

      17 በዘካርያስ ዘመን የነበሩት እስራኤላውያን ሰናኦር ክፋትን ለማስቀመጥ ተገቢ ቦታ እንደሆነ መገንዘብ አያዳግታቸውም። ዘካርያስም ሆነ በዘመኑ የነበሩት ሌሎች አይሁዳውያን ባቢሎን ክፋት የነገሠባት ቦታ እንደሆነች በገዛ ዓይናቸው ተመልክተዋል። በሥነ ምግባር ባዘቀጠችውና በጣዖት አምልኮ በተሞላችው በዚህች ከተማ ውስጥ ያደጉት እነዚህ አይሁዳውያን በዙሪያቸው ያለው አረማዊ ሥርዓት ተጽዕኖ እንዳያሳድርባቸው በየቀኑ ትግል ማድረግ ነበረባቸው። ይሖዋ ንጹሑን አምልኮ ከክፋት እንደሚጠብቅ ዋስትና የሚሰጠው ይህ ራእይ በእርግጥም ትልቅ እፎይታ አምጥቶላቸው መሆን አለበት!

      18 በተጨማሪም ይህ ራእይ አይሁዳውያኑ፣ የሚያቀርቡት አምልኮ ከክፋት የጸዳ እንዲሆን የማድረግ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስገንዝቧቸዋል። ክፋት በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ሰርጎ እንዲገባና በመካከላቸው እንዲኖር እንደማይፈቀድለት ደግሞም ሊፈቀድለት እንደማይገባ ግልጽ ነው። ጥበቃና ፍቅራዊ እንክብካቤ በምናገኝበት እንዲሁም ንጹሕ በሆነው የአምላክ ድርጅት ውስጥ የታቀፍን እንደመሆናችን መጠን ይህ ንጽሕና ተጠብቆ እንዲቀጥል የማድረግ ኃላፊነት አለብን። ታዲያ የይሖዋ ድርጅት ምንጊዜም ንጹሕ እንዲሆን የማድረግ ተነሳሽነት አለን? በመንፈሳዊ ገነታችን ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ክፋት ቦታ የለውም።

  • ዘካርያስ ካያቸው ራእዮች ምን ትምህርት እናገኛለን?
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017 | ጥቅምት
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ