-
“ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥር
-
-
1, 2. (ሀ) ይሖዋ በዘመናችን ምን እንደሚከናወን ተናግሯል? (ለ) በዚህ ርዕስ ሥር ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን? (በመግቢያው ላይ ያለውን ሥዕል ተመልከት።)
ይሖዋ የምንኖርበትን ዘመን አስመልክቶ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፦ “በዚያን ጊዜ ከብሔራት ቋንቋዎች ሁሉ የተውጣጡ አሥር ሰዎች የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ ‘አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን’ ይላሉ።” (ዘካ. 8:23) በዚህ ምሳሌያዊ አገላለጽ ላይ እንደተጠቀሱት አሥር ሰዎች ሁሉ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ክርስቲያኖችም “የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው” ይዘዋል። ይሖዋ ቅቡዓኑን እየባረካቸው እንደሆነ ስለሚያውቁ በመንፈስ ከተቀቡት ‘የአምላክ እስራኤል’ አባላት ጋር መተባበራቸው ያኮራቸዋል።—ገላ. 6:16
-
-
“ከእናንተ ጋር እንሄዳለን”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2016 | ጥር
-
-
4. በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ያሉትን የሁሉንም የመንፈሳዊ እስራኤል አባላት ስም ማወቅ የማይቻል ከሆነ ከእነሱ ጋር ‘መሄድ’ የምንችለው እንዴት ነው?
4 ታዲያ የሌሎች በጎች አባላት በዛሬው ጊዜ በምድር ላይ ያሉትን የሁሉንም የመንፈሳዊ እስራኤል አባላት ስም ማወቅ የማይችሉ ከሆነ ከእነሱ ጋር ‘መሄድ’ የሚችሉት እንዴት ነው? በዘካርያስ ላይ የሚገኘው ትንቢት ምሳሌያዊዎቹን አሥር ሰዎች በተመለከተ ምን እንደሚል ልብ በል። እነዚህ ሰዎች “የአንድን አይሁዳዊ ልብስ አጥብቀው በመያዝ ‘አምላክ ከእናንተ ጋር መሆኑን ስለሰማን ከእናንተ ጋር እንሄዳለን’ ይላሉ።” እዚህ ላይ የተጠቀሰው አይሁዳዊ አንድ ብቻ ቢሆንም “እናንተ” ከሚለው ተውላጠ ስም ማየት እንደሚቻለው ሐሳቡ የሚያመለክተው ብዙ ሰዎችን ነው። እንግዲያው እዚህ ላይ የተገለጸው አይሁዳዊ አንድን ሰው ሳይሆን አንድን ቡድን የሚያመለክት ነው! በመሆኑም አይሁዳዊ ተብለው የተገለጹትን ቅቡዓን በግለሰብ ደረጃ አውቀን ከእያንዳንዳቸው ጋር መሄድ አያስፈልገንም። ከዚህ ይልቅ እነዚህን ሰዎች ያቀፈውን ቡድን ለይተን ማወቅና መደገፍ ይኖርብናል። ቅዱሳን መጻሕፍት አንድን ግለሰብ እንድንከተል ፈጽሞ አያበረታቱንም። ምክንያቱም መሪያችን ኢየሱስ ነው።—ማቴ. 23:10
-