-
“እኔ . . . በልቤ ትሑት ነኝ”“ተከታዬ ሁን”
-
-
ምዕራፍ ሦስት
“እኔ . . . በልቤ ትሑት ነኝ”
“እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል”
1-3. ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም የገባው በምን ዓይነት ሁኔታ ነው? በዚያ ከነበሩት ተመልካቾች አንዳንዶቹ ሊገረሙ የሚችሉት ለምንድን ነው?
ኢየሩሳሌም አንድ አስደሳች ክንውን በጉጉት እየተጠባበቀች ነው። አንድ ታላቅ ሰው እየመጣ ነው! ከከተማዋ ውጭ፣ ሰዎች በመንገዱ ዳር ተሰብስበዋል። ሰዎቹ የሚጠብቁትን ግለሰብ ለመቀበል በጣም ጓጉተዋል፤ ምክንያቱም አንዳንዶች ይህ ሰው የንጉሥ ዳዊት ወራሽና የእስራኤል ሕጋዊ ገዢ እንደሆነ እየተናገሩ ነው። ብዙዎቹ የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ወጥተዋል፤ ሌሎቹ ደግሞ መንገዱን ለማሳመር መደረቢያቸውንና የዛፍ ቅርንጫፎችን በመንገዱ ላይ ያነጥፋሉ። (ማቴዎስ 21:7, 8፤ ዮሐንስ 12:12, 13) ‘ይህ ሰው ወደ ከተማዋ የሚገባው በምን ዓይነት ሁኔታ ይሆን?’ የሚለው ጥያቄ ወደ አእምሯቸው ሳይመጣ አልቀረም።
2 አንዳንዶች በብዙ አጀብ ይመጣል ብለው አስበው ሊሆን ይችላል። ከዚህ ቀደም በከፍተኛ ክብር ወደ ከተማዋ የገቡ ታላላቅ ሰዎችን እንደሚያውቁ ጥርጥር የለውም። ለምሳሌ የንጉሥ ዳዊት ልጅ አቢሴሎም፣ ንጉሥ መሆኑን አዋጅ ባስነገረበት ወቅት ከሠረገላው ፊት ፊት የሚሮጡ 50 ሰዎችን አዘጋጅቶ ነበር። (2 ሳሙኤል 15:1, 10) የሮሙ ገዢ ጁሊየስ ቄሳር እንዲደረግለት ያዘዘው ዝግጅት ደግሞ ከዚህም የበለጠ ድምቀት ያለው ነው፤ ይህ ገዢ የድል ሰልፈኞችን እየመራ ወደ ሮም የፖለቲካ ማዕከል የተጓዘው፣ መብራት በተሸከሙ 40 ዝሆኖች ታጅቦ ነበር! የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እየተጠባበቁት ያሉት ሰው ግን ከእነዚህ ሁሉ የሚበልጥ ነው። የተሰበሰበው ሕዝብ ተረዳውም አልተረዳው ይህ ሰው ሲጠበቅ የነበረው መሲሕ አዎ፣ እስከ ዛሬ ከኖሩት ሰዎች ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው ነው። ይሁንና ወደፊት ንጉሥ የሚሆነው ይህ ሰው ብቅ ሲል አንዳንዶቹ ሳይገረሙ አይቀሩም።
3 ሰውየው ሲመጣ ሠረገላም ሆነ ከሠረገላ ፊት ፊት የሚሮጡ ሰዎች፣ ፈረሶች ወይም ዝሆኖች አልነበሩም። ኢየሱስ የመጣው ዝቅ ተደርጋ በምትታየው የጭነት እንስሳ ይኸውም በአህያa ላይ ተቀምጦ ነው። እሱም ሆነ የተቀመጠባት አህያ በተለያዩ ጌጣ ጌጦች አላሸበረቁም። በአህያዋ ጀርባ ላይ ያለው የተንቆጠቆጠ ኮርቻ ሳይሆን የኢየሱስ ተከታዮች ልብስ ነው። ከኢየሱስ በጣም ያነሰ ክብር ያላቸው ሰዎች ትልቅ ዝግጅትና ድምቀት ያለው ሥርዓት እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ እሱ ግን እንዲህ ባለ ያልተጋነነ ሁኔታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት የመረጠው ለምንድን ነው?
4. መጽሐፍ ቅዱስ መሲሐዊው ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም የሚገባበትን ሁኔታ የሚገልጽ ምን ትንቢት ይዟል?
4 ኢየሱስ የሚከተለው ትንቢት ፍጻሜውን እንዲያገኝ እያደረገ ነው፦ “እጅግ ሐሴት አድርጊ። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ። እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል። እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤ ትሑት ነው፤ ደግሞም በአህያ . . . ላይ ይቀመጣል።” (ዘካርያስ 9:9) ይህ ትንቢት በአምላክ የተቀባው መሲሕ፣ መለኮታዊ ሹመት ያገኘ ንጉሥ መሆኑን ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንደሚገልጥ የሚያሳይ ነው። በተጨማሪም ኢየሱስ በአህያ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባቱ በልቡ ውስጥ ያለውን አንድ ግሩም ባሕርይ ማለትም ትሕትናውን ያሳያል።
-
-
“እኔ . . . በልቤ ትሑት ነኝ”“ተከታዬ ሁን”
-
-
a አንድ የማመሣከሪያ ጽሑፍ ይህን ሁኔታ በተመለከተ ባቀረበው ዘገባ ላይ እነዚህ እንስሳት “ዝቅ ተደርገው የሚታዩ” እንደሆኑ ተናግሯል፤ አክሎም “ቀርፋፎች፣ አስቸጋሪዎች፣ ድሃ የሆኑ ሰዎች ለአንዳንድ ተራ ሥራዎች የሚጠቀሙባቸውና ብዙም የማይማርኩ” መሆናቸውን ገልጿል።
-