የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ነሐሴ 15
    • ሥሩ ጉዳት ቢያገኘው የቀሩት የዛፉ ክፍሎችም ይጎዳሉ። (ከማቴዎስ 3:10፤ 13:6 ጋር አወዳድር።) ስለሆነም ሚልክያስ “የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፣ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፣ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር” ሲል ጽፏል። (ሚልክያስ 4:1) ትርጉሙ ሙሉ በሙሉ መቆረጥ ማለት እንደሆነ ግልጽ ነው። ወላጆች (ሥሮች) ይቆረጣሉ፤ ልጆቻቸውም (ቅርንጫፎቻቸውም) አብረው ይቆረጣሉ ማለት ነበር።a ይህም ወላጆች ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆቻቸው ያለባቸውን ኃላፊነት ያጎላል። ለአካለ መጠን ያልደረሱ ልጆች የወደፊት ዕድል የሚወሰነው ወላጆቻቸው በአምላክ ፊት ባላቸው አቋም መሠረት ነው።—1 ቆሮንቶስ 7:14

      በኢሳይያስ 37:31 እና በሚልክያስ 4:1 ላይ ያሉት አገላለጾች የዋናዎቹ ቅርንጫፎች (ወይም በንዑስ ቅርንጫፎች ላይ ያሉት ፍሬዎች) ሕይወት የተመካው በሥሩ ላይ መሆኑን ያሳያሉ። ኢየሱስ “የእሴይ ሥር” ወይም “የዳዊት ሥር” የሆነበትን ምክንያት ለመረዳት የሚያስችለን ቁልፍ ነገር ይህ ነው።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ነሐሴ 15
    • a በጥንታዊ የፊንቃውያን አንድ መቃብር ሐውልት ላይ የተቀረጸ ጽሑፍ ተመሳሳይ አባባል ተጠቅሟል። መቃብሩን ስለሚከፍቱት ሰዎች “ከታች ሥር ከላይም ፍሬ አይኑራቸው!” የሚሉ የእርግማን ቃላት ተጽፈውበት ነበር።—ዊተስ ቴስታሜንተም፣ ሚያዝያ 1961

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ