የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይሖዋ የክህደትን ጎዳና ይጠላል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ግንቦት 1
    • 16, 17. አንዳንዶች የተከተሉት የክህደት ጎዳና ምንድን ነው?

      16 ሚልክያስ ቀጥሎ ሁለተኛውን የክህደት ዓይነት ይኸውም የትዳር ጓደኛን በተለይም ፍትሐዊ ባልሆነ ምክንያት በመፍታት መበደልን ያነሳል። ምዕራፍ 2 ቁጥር 14 እንዲህ ይላል:- “ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና [“በእርስዋ ላይ ክህደት ፈጽመሃልና፣” NW ] እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው።” አይሁዳውያን ባሎች በሚስቶቻቸው ላይ ክህደት በመፈጸም የይሖዋ መሠዊያ ‘በእንባ እንዲርስ’ አድርገው ነበር። (ሚልክያስ 2:​13) እነዚህ ወንዶች ወጣት ሴቶችን ወይም የአሕዛብ ሴቶችን ለማግባት ሲሉ በረባ ባልረባው የልጅነት ሚስቶቻቸውን ያላግባብ ይፈቱ ነበር። ምግባረ ብልሹ የሆኑት ካህናትም ይህን በዝምታ ተመልክተዋል! ሆኖም ሚልክያስ 2:​16 “መፋታትን እጠላለሁ፣ ይላል የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር” በማለት ይናገራል። ከጊዜ በኋላ ኢየሱስ፣ በደል የተፈጸመበት የትዳር ጓደኛ ፈትቶ ሌላ ለማግባት የሚያስችለው ብቸኛው ምክንያት የጾታ ብልግና እንደሆነ ተናግሯል።​—⁠ማቴዎስ 19:​9

  • ይሖዋ የክህደትን ጎዳና ይጠላል
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ግንቦት 1
    • 18. ሚልክያስ ክህደትን አስመልክቶ የሰጠው ምክር በዛሬው ጊዜ የሚሠራው በምን መንገድ ነው?

      18 ይህ ምክር ዛሬም ከጥንቱ ባላነሰ ሁኔታ እንደሚሠራ ግልጽ ነው። አንዳንዶች አምላክ በጌታ ብቻ እንዲያገቡ የሰጠውን መመሪያ ችላ ማለታቸው የሚያሳዝን ነው። እንዲሁም አንዳንዶች ጋብቻቸውን ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት አለመቀጠላቸው የሚያሳዝን ነው። ከዚህ ይልቅ ሌላ ሰው ለማግባት ሲሉ ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ ፍቺ በመፈጸም አምላክ የሚጠላውን ለማድረጋቸው ሰበብ ወይም ማመካኛ ለማግኘት ይጥራሉ። ይህን የመሰለ ነገር በማድረግ ‘ይሖዋን አታክተውታል።’ በሚልክያስ ዘመን መለኮታዊውን መመሪያ ችላ ይሉ የነበሩ ሰዎች የይሖዋ አመለካከት ተገቢ እንዳልሆነ ይሰማቸው ነበር። እንዲያውም “የፍርድ አምላክ ወዴት አለ?” እስከማለት ደርሰዋል። እንዴት ያለ የተጣመመ አስተሳሰብ ነው! እንዲህ ባለው ወጥመድ ውስጥ እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ።​—⁠ሚልክያስ 2:​17

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ