-
የሚልክያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ታኅሣሥ 15
-
-
3:10—“ዐሥራቱን ሁሉ” እንዲያስገቡ የተሰጠው መመሪያ ያለንን ሁሉ ለይሖዋ መስጠትን ያመለክታል? የኢየሱስ መሞት የሙሴ ሕግ እንዲቀር ስላደረገ አምላክ በዛሬው ጊዜ የገንዘብ ዐሥራት እንድንሰጥ አይጠብቅብንም። ያም ሆኖ ዐሥራት ምሳሌያዊ ትርጉም አለው። (ኤፌሶን 2:15) ዐሥራት ያለንን ሁሉ ለይሖዋ መስጠትን አያመለክትም። እስራኤላውያን ዐሥራት የሚያስገቡት በየዓመቱ ሲሆን እኛ ግን ሁለንተናችንን ለይሖዋ የሰጠነው አንድ ጊዜ ነው፤ ይህም የሆነው ራሳችንን ለእሱ ወስነን በውኃ ስንጠመቅ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያለን ነገር ሁሉ የይሖዋ ነው። እንደዚያም ሆኖ ካለን ነገር የተወሰነውን ለእሱ አገልግሎት በማዋል በምሳሌያዊ ሁኔታ ዐሥራት እንድናስገባ ፈቅዶልናል። ይህም ሁኔታችን እንደፈቀደልንና ልባችን እንዳነሳሳን የምንሰጠው ነገር ነው። ለይሖዋ የምናቀርበው መሥዋዕት ስለ አምላክ መንግሥት በመስበኩና ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ጊዜያችንን፣ ጉልበታችንንና ጥሪታችንን መጠቀምን ይጨምራል። ከዚህም በላይ በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ መገኘትን፣ የታመሙና በዕድሜ የገፉ የእምነት ባልንጀሮቻንን መጠየቅን እንዲሁም እውነተኛውን አምልኮ በገንዘብ መደገፍንም ያጠቃልላል።
-
-
የሚልክያስ መጽሐፍ ጎላ ያሉ ነጥቦችመጠበቂያ ግንብ—2007 | ታኅሣሥ 15
-
-
3:10፦ ለይሖዋ ምርጣችንን አለመስጠት የእሱን በረከት እንድናጣ ያደርገናል።
-