የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘በቃሌ ኑሩ’
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
    • 16. (ሀ) እሾህ በወረሰው አፈር የተመሰሉት ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? (ለ) በሦስቱ የወንጌል ዘገባዎች መሠረት እሾሁ የምን ምሳሌ ነው?​—⁠የግርጌ ማስታወሻውን ተመልከት።

      16 እሾህ በወረሰው አፈር የተመሰሉት ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? ኢየሱስ እንዲህ ሲል ገልጿል:- “እነዚህ የሚሰሙት ናቸው፤ መንገዳቸውንም ሄደው በሕይወት ዘመን በአሳብና በባለ ጠግነት ምቾት ይታነቃሉ፣ ሙሉ ፍሬም አያፈሩም።” (ሉቃስ 8:14) ዘሪው የዘራው ዘርና እሾሁ አብረው እንደሚያድጉ ሁሉ አንዳንድ ግለሰቦችም የአምላክን ቃልና የዚህን ዓለም ‘አሳብና የባለ ጠግነት ምቾት’ እኩል ለማስተናገድ ይሞክራሉ። የአምላክ ቃል እውነት በልባቸው ውስጥ ተዘርቷል፤ ሆኖም ትኩረትን የሚከፋፍሉ ሌሎች ጉዳዮች ለእድገት የሚያስፈልገውን ነገር ይሻሙታል። ምሳሌያዊው ልባቸው ተከፍሏል። (ሉቃስ 9:​57-62) ይህም ከአምላክ ቃል ባነበቡት ነገር ላይ በጸሎት የሚያሰላስሉበት በቂ ጊዜ እንዳይኖራቸው ያደርጋቸዋል። የአምላክን ቃል በተሟላ ሁኔታ ስለማይረዱ ለመጽናት የሚያስችል ልባዊ አድናቆት ይጎድላቸዋል። ውሎ አድሮ መንፈሳዊ ፍላጎታቸው መንፈሳዊ ባልሆኑ ነገሮች ይሸፈንና በመጨረሻም ‘ሙሉ በሙሉ ይታነቃሉ።’c ይሖዋን በሙሉ ልባቸው የማይወድዱት ሰዎች መጨረሻቸው ምንኛ አሳዛኝ ነው!​—⁠ማቴዎስ 6:​24፤ 22:​37

      17. ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ የገለጸው ምሳሌያዊ እሾህ እንዳያንቀን በሕይወታችን ውስጥ ምን ምርጫዎችን ማድረግ ይኖርብናል?

      17 ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ ለመንፈሳዊ ጉዳዮች ቅድሚያ በመስጠት በዚህ ዓለም አሳብና ምቾት እንዳንታነቅ ጥንቃቄ ማድረግ እንችላለን። (ማቴዎስ 6:​31-33፤ ሉቃስ 21:​34-36) መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ባነበብነው ነገር ላይ ማሰላሰል ቸል ሊባል አይገባውም። አኗኗራችንን በተቻለን መጠን ቀላል የምናደርግ ከሆነ አእምሯችንን ሰብሰብ አድርገን እየጸለይን ለማሰላሰል የሚያስችል ተጨማሪ ጊዜ ማግኘት እንችላለን። (1 ጢሞቴዎስ 6:​6-8) በልባቸው ላይ የተዘራው ምሳሌያዊ ዘር በቂ ምግብ፣ የፀሐይ ብርሃንና ቦታ አግኝቶ ፍሬ እንዲያፈራ እሾሁን የሚነቅሉ ማለትም አኗኗራቸውን ቀላል የሚያደርጉ የአምላክ አገልጋዮች የይሖዋን በረከት ያገኛሉ። የ26 ዓመቷ ሳንድራ “በእውነት ውስጥ በመኖሬ ስላገኘኋቸው በረከቶች መለስ ብዬ ሳስብ ይህ ዓለም ከዚህ በረከት ጋር የሚተካከል ምንም ነገር ሊሰጠኝ እንደማይችል እገነዘባለሁ!” ብላለች።​—⁠መዝሙር 84:​11

  • ‘በቃሌ ኑሩ’
    መጠበቂያ ግንብ—2003 | የካቲት 1
    • c ሦስቱ የወንጌል ዘገባዎች ‘የዚህ ዓለም አሳብ፣’ “የባለጠግነት ማታለል፣” “የሌላውም ነገር ምኞት፣” እና ‘ተድላና ደስታ’ በማለት እንደገለጹት ሁሉ ኢየሱስ በተናገረው ምሳሌ ውስጥ የተጠቀሰው ዘር የታነቀው በዚህ ዓለም አሳብ እንዲሁም ተድላና ደስታ ነው።​—⁠ማርቆስ 4:​19፤ ማቴዎስ 13:​22፤ ሉቃስ 8:​14 አ.መ.ት ፤ ኤርምያስ 4:​3, 4

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ