የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 5. በምሳሌው ላይ የተገለጸው ጠላት ማን ነው? በእንክርዳዱስ የተመሰሉት እነማን ናቸው?

      5 ጠላት የተባለው ማን ነው? እንክርዳድ የተባሉትስ እነማን ናቸው? ኢየሱስ ጠላት የተባለው “ዲያብሎስ ነው” በማለት ተናግሯል። እንክርዳዶቹ ደግሞ “የክፉው ልጆች” እንደሆኑ ተገልጿል። (ማቴ. 13:25, 38, 39) እንክርዳድ መርዛማ እህል ሲሆን በቡቃያነት ደረጃ ከስንዴ ጋር በጣም ይመሳሰላል። የመንግሥቱ ልጆች እንደሆኑ ቢናገሩም እውነተኛ ፍሬ የማያፈሩ አስመሳይ ክርስቲያኖች በእንክርዳድ መመሰላቸው ምንኛ የተገባ ነው! እንደ እውነቱ ከሆነ፣ የክርስቶስ ተከታይ እንደሆኑ የሚናገሩት እነዚህ ግብዝ ክርስቲያኖች የሰይጣን ዲያብሎስ ‘ዘር’ ክፍል ናቸው።—ዘፍ. 3:15

  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • 7. አንዳንድ ስንዴዎች ተቀይረው እንክርዳድ ሆነው ነበር? አብራራ።

      7 ኢየሱስ እዚህ ምሳሌ ላይ ስንዴው ተቀይሮ እንክርዳድ ይሆናል አላለም፤ ከዚህ ይልቅ እሱ የተናገረው በስንዴው መካከል እንክርዳድ እንደተዘራ ነው። በመሆኑም ይህ ምሳሌ ከእውነት የወጡትን እውነተኛ ክርስቲያኖች የሚያመለክት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ሰይጣን ክፉ ሰዎች ወደ ክርስቲያን ጉባኤ ሰርገው እንዲገቡ በማድረግ ሆን ብሎ ጉባኤውን ለመበከል የሚያደርገውን ጥረት ያመለክታል። የመጨረሻ ሐዋርያ የነበረው ዮሐንስ ዕድሜው በገፋበት ወቅት ክህደቱ በግልጽ መታየት ጀምሮ ነበር።—2 ጴጥ. 2:1-3፤ 1 ዮሐ. 2:18

  • ‘ጻድቃን እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ’
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 15
    • ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የመከር ወቅት

      10, 11. (ሀ) የመከሩ ወቅት መቼ ነው? (ለ) ምሳሌያዊው ስንዴ ወደ ይሖዋ ጎተራ እየገባ ያለው እንዴት ነው?

      10 ኢየሱስ “መከሩ የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ሲሆን አጫጆቹ ደግሞ መላእክት ናቸው” በማለት ተናግሯል። (ማቴ. 13:39) በዚህ ክፉ ሥርዓት የመጨረሻ ቀኖች የመለየቱ ሥራ ይካሄዳል፤ ይኸውም የመንግሥቱ ልጆች ተሰብስበው በእንክርዳድ ከተመሰሉት ሰዎች ይለያሉ። ይህን በተመለከተ ሐዋርያው ጴጥሮስ እንደሚከተለው ብሏል፦ “ፍርድ ከአምላክ ቤት የሚጀምርበት አስቀድሞ የተወሰነው ጊዜ ይህ ነው። እንግዲህ ፍርድ በቅድሚያ በእኛ የሚጀምር ከሆነ ለአምላክ ምሥራች ታዛዥ ያልሆኑ ሰዎች መጨረሻ ምን ይሆን?”—1 ጴጥ. 4:17

      11 የመጨረሻዎቹ ቀኖች ወይም “የዚህ ሥርዓት መደምደሚያ” ከጀመረ ብዙም ሳይቆይ እውነተኛ ክርስቲያኖች እንደሆኑ በሚናገሩ ሰዎች ላይ ፍርድ ጀምሯል፤ ይህ ፍርድ እነዚህ ሰዎች በእርግጥ “የመንግሥቱ ልጆች” ወይም “የክፉው ልጆች” መሆናቸውን ያረጋግጣል። “በመጀመሪያ” ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፤ “ከዚያም” በመከሩ ወቅት መጀመሪያ ላይ የመንግሥቱ ልጆች በአንድነት ተሰበሰቡ። (ማቴ. 13:30) ታዲያ ምሳሌያዊው ስንዴ ወደ ይሖዋ ጎተራ እየገባ ያለው እንዴት ነው? እነዚህ የተሰበሰቡት ክርስቲያኖች የአምላክን ሞገስና ጥበቃ በሚያገኙበት በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ታቅፈዋል ወይም በሰማይ ሽልማታቸውን አግኝተዋል።

      12. መከሩ የሚቀጥለው ለምን ያህል ጊዜ ነው?

      12 ፍርዱ የሚቆየው ለምን ያህል ጊዜ ነው? ኢየሱስ ስለ መከሩ ሲናገር “ወቅት” የሚለውን ቃል መጠቀሙ ፍርዱ ረዘም ላለ ጊዜ የሚቀጥል መሆኑን ያሳያል። (ራእይ 14:15, 16) ለእያንዳንዱ ቅቡዕ የሚሰጠው ፍርድ በመጨረሻው ዘመን ሁሉ ይቀጥላል። ይህ ፍርድ የሚጠናቀቀው ቅቡዓኑ ለመጨረሻ ጊዜ ማኅተም ሲደረግባቸው ነው።—ራእይ 7:1-4

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ