-
“ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
-
-
13. ራእይ 18:7 ሕዝበ ክርስትናን ጨምሮ ጋለሞታይቱ ወይም ታላቂቱ ባቢሎን በአሁኑ ጊዜ ያላትን አመለካከት የሚገልጸው እንዴት ነው?
13 ሦስተኛው ማልቀስና ጥርስ ማፋጨት ነው። መላእክቱ እንክርዳዱን በየነዶው ካሰሩ በኋላ ምን ይከናወናል? ኢየሱስ የእንክርዳዱ ክፍል የሆኑት፣ ስለሚገኙበት ሁኔታ ሲናገር “በዚያም ያለቅሳሉ፣ በሐዘንም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ” ብሏል። (ማቴ. 13:42) ታዲያ ይህ ሁኔታ በአሁኑ ጊዜ እየተፈጸመ ነው? በፍጹም። የጋለሞታይቱ ክፍል የሆነችው ሕዝበ ክርስትና ዛሬም “ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ፤ መበለትም አይደለሁም፤ ሐዘንም ፈጽሞ አይደርስብኝም” ብላ ታስባለች። (ራእይ 18:7) በእርግጥም ሕዝበ ክርስትና ሥልጣን እንዳላት ይሰማታል፤ እንዲያውም በፖለቲካ መሪዎች ላይ ‘እንደተቀመጠች ንግሥት’ አድርጋ ራሷን ትቆጥራለች። በመሆኑም በእንክርዳድ የተመሰሉት ሐሰተኞቹ ክርስቲያኖች በአሁኑ ጊዜ እያለቀሱ ሳይሆን እየተኩራሩ ነው። ይሁን እንጂ ይህ ሁኔታ የሚለወጥበት ጊዜ ቀርቧል።
ሕዝበ ክርስትና ከፖለቲካ መሪዎች ጋር ያላት ወዳጅነት በቅርቡ ያከትማል (አንቀጽ 13ን ተመልከት)
14. (ሀ) አስመሳይ ክርስቲያኖች ‘ጥርሳቸውን የሚያፋጩት’ መቼ ነው? ለምንስ? (ለ) ማቴዎስ 13:42ን በተመለከተ ያገኘነው አዲሱ መረዳት ከመዝሙር 112:10 ጋር የሚስማማው እንዴት ነው? (ተጨማሪ መረጃውን ተመልከት።)
14 በተደራጀ መንገድ የሚንቀሳቀሱ የሐሰት ሃይማኖቶች በሙሉ በታላቁ መከራ ወቅት ሲጠፉ እነሱን ሲደግፉ የነበሩ ሁሉ መሸሸጊያ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ ሆኖም ለመደበቅ የሚያስችል አስተማማኝ ቦታ ማግኘት አይችሉም። (ሉቃስ 23:30፤ ራእይ 6:15-17) ከጥፋቱ ማምለጥ እንደማይችሉ ሲገነዘቡ ተስፋ በመቁረጥ ያለቅሳሉ፤ በንዴትም “ጥርሳቸውን ያፋጫሉ።” ኢየሱስ ስለ ታላቁ መከራ በተናገረው ትንቢት ላይ እንደተገለጸው ጨለማ በሆነው በዚያ ወቅት “ደረታቸውን ይደቃሉ።”e—ማቴ. 24:30፤ ራእይ 1:7
15. እንክርዳዱ ምን ይሆናል? ይህ የሚሆነውስ መቼ ነው?
15 አራተኛው ወደ እቶን እሳት መጣል ነው። በየነዶው የታሰረው እንክርዳድ ምን ይሆናል? መላእክቱ ‘ወደ እቶን እሳቱ ይጥሉታል።’ (ማቴ. 13:42) ይህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ መጥፋትን ያመለክታል። በመሆኑም የሐሰት ሃይማኖት ድርጅቶችን ሲደግፉ የነበሩ ሁሉ በታላቁ መከራ የመጨረሻ ምዕራፍ ማለትም በአርማጌዶን ይጠፋሉ።—ሚል. 4:1
-
-
“ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ”መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
-
-
e አንቀጽ 14፦ ይህ ሐሳብ ማቴዎስ 13:42ን አስመልክቶ ከዚህ በፊት የነበረንን መረዳት የሚያስተካክል ነው። ቀደም ሲል በጽሑፎቻችን ላይ “የመንግሥቱ ልጆች” የአስመሳይ ክርስቲያኖችን ማንነት ስላጋለጡ ይኸውም “የክፉው ልጆች” መሆናቸውን ስለመሠከሩ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት እያለቀሱና ጥርሳቸውን እያፋጩ እንደነበረ ተገልጾ ነበር። (ማቴ. 13:38) ይሁንና ጥርስን ማፋጨት ከጥፋት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ማስተዋል ይገባናል።—መዝ. 112:10
-