የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስለ መንግሥቱ የተነገሩ ምሳሌዎች
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • አንድ ሰው በእርሻ ውስጥ የተደበቀ ሀብት አገኘ
      አንድ ተጓዥ ነጋዴ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ዕንቁ አገኘ

      ኢየሱስ በመቀጠል ለደቀ መዛሙርቱ ሦስት ተጨማሪ ምሳሌዎችን ነገራቸው። በመጀመሪያ እንዲህ አለ፦ “መንግሥተ ሰማያት በእርሻ ውስጥ ከተደበቀ ውድ ሀብት ጋር ይመሳሰላል፤ አንድ ሰው ባገኘው ጊዜ ሸሸገው፤ ከመደሰቱም የተነሳ ሄዶ ያለውን ሁሉ በመሸጥ እርሻውን ገዛው።”—ማቴዎስ 13:44

  • ስለ መንግሥቱ የተነገሩ ምሳሌዎች
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • በሁለቱም ምሳሌዎች ላይ ኢየሱስ ያጎላው በጣም ውድ ዋጋ ያለውን ነገር ለማግኘት ሲባል መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆንን ነው። ነጋዴው፣ ከፍተኛ ዋጋ ያለው ዕንቁ ለመግዛት ሲል “ያለውን ሁሉ” ወዲያውኑ ሸጧል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ውድ ስለሆነው ዕንቁ የተሰጠውን ምሳሌ መረዳት ይችላሉ። በእርሻ ውስጥ የተደበቀ ውድ ሀብት ያገኘው ሰውም ይህን ሀብት እጁ ለማስገባት ሲል ‘ያለውን ሁሉ ሸጧል።’ ሁለቱም ሰዎች ውድ ዋጋ ያለው ነገር ይኸውም የራሳቸው ሊያደርጉትና ትልቅ ቦታ ሊሰጡት የሚገባ ነገር አግኝተዋል። የወሰዱት እርምጃ አንድ ሰው መንፈሳዊ ጥማቱን ለማርካት ሲል ከሚከፍለው መሥዋዕት ጋር ሊነጻጸር ይችላል። (ማቴዎስ 5:3) ኢየሱስ እነዚህን ምሳሌዎች ሲናገር ከሰሙት ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ፣ መንፈሳዊ ጥማታቸውን ለማርካትና የእሱ እውነተኛ ተከታዮች ለመሆን ሲሉ ከፍተኛ መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኛ መሆናቸውን አሳይተዋል።—ማቴዎስ 4:19, 20፤ 19:27

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ