-
ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷልበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
እርማት ቢሰጠውም ታማኝ ሆኗል
11. ኢየሱስ ተከታዮቹን ወዴት ይዟቸው ሄደ? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)
11 ውጥረት የበዛበት ያ ቀን ካለፈ ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ ሐዋርያቱንና የተወሰኑ ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ረጅም ጉዞ አደረገ። በተስፋይቱ ምድር ሰሜናዊ ጫፍ ላይ የሚገኘው በበረዶ የተሸፈነው የሄርሞን ተራራ አናት፣ አንዳንድ ጊዜ ከገሊላ ባሕር እንኳ ይታያል። ኢየሱስና ተከታዮቹ ቂሳርያ ፊልጵስዩስ አቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች የሚወስደውን አቀበታማ መንገድ እየወጡ ሲሄዱ የተራራው ግዝፈት ይበልጥ ጎልቶ እየታየ ይሄዳል።b በስተ ደቡብ አቅጣጫ አብዛኛውን የተስፋይቱ ምድር ገጽታ ማየት በሚያስችለው በዚህ ማራኪ ቦታ ላይ ሳሉ ኢየሱስ ተከታዮቹን አንድ አስፈላጊ ጥያቄ ጠየቃቸው።
12, 13. (ሀ) ኢየሱስ ሕዝቡ ስለ እሱ ያለውን አመለካከት ማወቅ የፈለገው ለምንድን ነው? (ለ) ጴጥሮስ ለኢየሱስ የሰጠው መልስ እውነተኛ እምነት እንዳለው የሚያሳየው እንዴት ነው?
12 ኢየሱስ “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” አላቸው። ጴጥሮስ የዚህን ጥያቄ መልስ ለመስማት የጓጓውን ኢየሱስን ዓይን ዓይኑን ሲመለከት በዓይነ ሕሊናህ ይታይህ፤ በዚህ ጊዜም የጌታውን ደግነትና ጥልቅ የማስተዋል ችሎታ ማንበብ እንደቻለ መገመት አያዳግትም። ኢየሱስ አድማጮቹ ከተመለከቱትና ከሰሙት ነገር በመነሳት ምን መደምደሚያ ላይ እንደደረሱ ማወቅ ፈልጎ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም በኢየሱስ ማንነት ዙሪያ በሰፊው የሚነገሩትን የተሳሳቱ አመለካከቶች በመጥቀስ ለጥያቄው መልስ ሰጡ። ይሁንና ኢየሱስ በዚህ ብቻ አልረካም። የቅርብ ተከታዮቹም እንደ ሌሎቹ የተሳሳተ አመለካከት ይኖራቸው ይሆን? በመሆኑም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው።—ሉቃስ 9:18-20
-
-
ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷልበእምነታቸው ምሰሏቸው
-
-
b ኢየሱስና ተከታዮቹ ከባሕር ወለል በታች 210 ሜትር ገደማ ዝቅ ብሎ ከሚገኘው ከገሊላ ባሕር ዳርቻ ተነስተው ድንቅ የተፈጥሮ ውበት የተላበሰውን አካባቢ እያቋረጡ 350 ሜትር ገደማ ከፍታ ወዳለው ቦታ ተጓዙ፤ የመንገዱ ርዝመት 50 ኪሎ ሜትር ገደማ ይሆናል።
-