የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷል
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥር 1
    • እርማት ሲሰጠውም ታማኝ ሆኖ ቀጥሏል

      በቅፍርናሆም ያሳለፉት ውጥረት የበዛበት ያ ቀን ካለፈ ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ ሐዋርያቱንና አንዳንድ ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ሰሜን አቅጣጫ ረጅም ጉዞ አደረገ። በተስፋይቱ ምድር ሰሜናዊ ጫፍ ላይ የሚገኘው በበረዶ የተሸፈነው የሄርሞን ተራራ አናት፣ አንዳንድ ጊዜ ከርቀት ሌላው ቀርቶ ሰማያዊ ቀለም ካለው የገሊላ ባሕር ላይ እንኳ ይታያል። ቂሳርያ ፊልጵስዩስ አቅራቢያ ወዳሉት መንደሮች የሚወስደውን አቀበታማ መንገድ እየወጡ ሲሄዱ የተራራው ከፍታ ይበልጥ ጎልቶ እየታየ ይሄዳል።c አንድ ሰው ከዚህ አካባቢ ሆኖ ፊቱን ወደ ደቡብ አቅጣጫ ሲያዞር አብዛኛውን የተስፋይቱ ምድር ገጽታ ማየት ይችላል። ውብ መልክዓ ምድር ባለው በዚህ አካባቢ ሳሉ ኢየሱስ ተከታዮቹን አንድ አስፈላጊ ጥያቄ ጠየቃቸው።

      ኢየሱስ “ሕዝቡ እኔን ማን ይሉኛል?” ሲል ጠየቃቸው። ጴጥሮስ መልስ ለማግኘት የሚጓጉትን የኢየሱስን ዓይኖች ሲመለከት እስቲ በዓይነ ሕሊናችን ይታየን፤ ጴጥሮስ የጌታውን ዓይን ሲመለከት ደግነቱ እንዲሁም ማንም ሰው በቀላሉ ሊረዳው የሚችለውን ከፍተኛ የማስተዋል ችሎታውን እንደገና እንደተገነዘበ መገመት አያዳግትም። ኢየሱስ አድማጮቹ ከተመለከቱትና ከሰሙት ነገር በመነሳት ምን መደምደሚያ ላይ እንደደረሱ ማወቅ ፈልጎ ነበር። ደቀ መዛሙርቱም በኢየሱስ ማንነት ዙሪያ በሰፊው የሚነገሩትን የተሳሳቱ አመለካከቶች በመጥቀስ ለጥያቄው መልስ ሰጡ። ይሁንና ኢየሱስ በዚህ ብቻ አልረካም። የቅርብ ተከታዮቹም እንደ ሌሎቹ ስለ እሱ የተሳሳተ አመለካከት ይኖራቸው ይሆን? በመሆኑም “እናንተስ እኔን ማን ትሉኛላችሁ?” በማለት ጠየቃቸው።—ሉቃስ 9:18-22

  • ፈተናዎች ቢደርሱበትም ታማኝ መሆኑን አሳይቷል
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ጥር 1
    • c ኢየሱስና ተከታዮቹ 48 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚፈጀውን ይህን ጉዞ ያደረጉት ከገሊላ ባሕር ዳርቻዎች ይኸውም ከባሕር ወለል በታች 210 ሜትር ገደማ ከሆነ ዝቅተኛ ስፍራ ተነስተው ድንቅ የተፈጥሮ ውበት የተላበሰውን አካባቢ እያቋረጡ 350 ሜትር የሚጠጋ ከፍታ ወዳለው ቦታ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ