የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በተአምራዊ ሁኔታ ተለወጠ—ክርስቶስ በክብሩ ታየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ ከሄርሞን ተራራ 25 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በሚገኘው በቂሳርያ ፊልጵስዩስ ክልል ሕዝቡን እያስተማረ ሳለ የሚከተለውን አስገራሚ ሐሳብ ለሐዋርያቱ ተናገረ፦ “እውነት እላችኋለሁ፣ እዚህ ከቆሙት መካከል አንዳንዶች የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ እስኪያዩ ድረስ ፈጽሞ ሞትን አይቀምሱም።”—ማቴዎስ 16:28

      ደቀ መዛሙርቱ፣ ኢየሱስ ምን ማለቱ እንደሆነ ግራ ሳይገባቸው አልቀረም። ኢየሱስ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ አንድ ረጅም ተራራ ወጣ። ሦስቱ ሐዋርያት እንቅልፍ እንደተጫጫናቸው ስለተገለጸ ይህ የሆነው ምሽት ላይ ሳይሆን አይቀርም። ኢየሱስ እየጸለየ ሳለ በፊታቸው ተለወጠ። ሐዋርያቱ ፊቱ እንደ ፀሐይ ሲያበራና ልብሱም እንደ ብርሃን ሲያንጸባርቅ ወይም ነጭ ሲሆን ተመለከቱ።

  • በተአምራዊ ሁኔታ ተለወጠ—ክርስቶስ በክብሩ ታየ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ይህ ራእይ ኢየሱስንም ሆነ ሐዋርያቱን ምንኛ የሚያበረታታ ነው! ራእዩ ክርስቶስ በመንግሥቱ በክብር ሲመጣ የሚኖረውን ሁኔታ የሚያሳይ ናሙና ነው። ስለዚህ ኢየሱስ ቃል በገባው መሠረት ደቀ መዛሙርቱ “የሰው ልጅ በመንግሥቱ ሲመጣ” ተመልክተዋል ማለት ይቻላል። (ማቴዎስ 16:28) በተራራው ላይ እያሉ ‘ግርማውን በገዛ ዓይናቸው አይተዋል።’ ኢየሱስ፣ አምላክ የመረጠው ንጉሥ እንደሚሆን የሚያረጋግጥ ምልክት እንዲያሳያቸው ፈሪሳውያን ቢጠይቁትም እንዲህ ዓይነት ምልክት አልሰጣቸውም። በሌላ በኩል ግን የቅርብ ደቀ መዛሙርቱ፣ ኢየሱስ በተአምራዊ ሁኔታ ሲለወጥ አይተዋል፤ ይህ ራእይ ስለ መንግሥቱ የተነገሩ ትንቢቶች እንደሚፈጸሙ ያረጋግጣል። በመሆኑም ጴጥሮስ “ትንቢታዊው ቃል ይበልጥ ተረጋግጦልናል” በማለት ከጊዜ በኋላ ጽፏል።—2 ጴጥሮስ 1:16-19

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ