የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋን ድምፅ ስሙ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | መጋቢት
    • “እሱን ስሙት”

      7. በማቴዎስ 17:1-5 ላይ እንደተገለጸው ይሖዋ ከሰማይ የተናገረው በየትኛው አጋጣሚ ነው? ምን በማለትስ ተናግሯል?

      7 ማቴዎስ 17:1-5⁠ን አንብብ። ይሖዋ ለሁለተኛ ጊዜ ከሰማይ የተናገረው ኢየሱስ ‘በተለወጠበት’ ወቅት ነው። ኢየሱስ ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብና ከዮሐንስ ጋር ወደ አንድ ከፍ ያለ ተራራ ሄደ። በዚያም እነዚህ ሐዋርያት አስደናቂ ራእይ ተመለከቱ። የኢየሱስ ፊት በደማቁ አበራ፤ ልብሱም ማንጸባረቅ ጀመረ። ከዚያም ሙሴንና ኤልያስን የሚወክሉ ሁለት ሰዎች ተገልጠው ከኢየሱስ ጋር ከፊቱ ስለሚጠብቀው ሞትና ስለ ትንሣኤው ይነጋገሩ ጀመር። ሦስቱ ሐዋርያት “እንቅልፍ ተጫጭኗቸው” የነበረ ቢሆንም ይህን አስገራሚ ራእይ የተመለከቱት ሙሉ በሙሉ ነቅተው ነው። (ሉቃስ 9:29-32) ከዚያም ብሩህ ደመና ከጋረዳቸው በኋላ ከደመናው ውስጥ አንድ ድምፅ ሰሙ። ይህ ድምፅ የአምላክ ድምፅ ነበር! ይሖዋ፣ ኢየሱስ በተጠመቀበት ወቅት እንዳደረገው ሁሉ በዚህ ጊዜም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው” በማለት ልጁን እንደሚወደውና ደስ እንደሚሰኝበት ገለጸ። በዚህ ጊዜ ግን “እሱን ስሙት” በማለት አክሎ ተናገረ።

  • የይሖዋን ድምፅ ስሙ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019 | መጋቢት
    • 9. ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ምን ጠቃሚ ምክር ሰጥቷቸዋል?

      9 “እሱን ስሙት።” ይሖዋ ልጁ የተናገራቸውን ነገሮች እንድንሰማና እንድንታዘዝ ያለውን ፍላጎት ግልጽ አድርጓል። ኢየሱስ ምድር ላይ ሳለ ምን ነገሮችን ተናግሯል? ኢየሱስ ልንሰማቸው የሚገቡ በርካታ ነገሮችን ተናግሯል! ለምሳሌ ተከታዮቹ የመንግሥቱን ምሥራች መስበክ እንዳለባቸው ፍቅር በሚንጸባረቅበት መንገድ አስተምሯቸዋል፤ እንዲሁም ነቅተው እንዲጠብቁ በተደጋጋሚ አሳስቧቸዋል። (ማቴ. 24:42፤ 28:19, 20) በተጨማሪም ሕይወት ለማግኘት ከፍተኛ ተጋድሎ እንዲያደርጉ የመከራቸው ከመሆኑም ሌላ ተስፋ እንዳይቆርጡ አበረታቷቸዋል። (ሉቃስ 13:24) ከዚህም በላይ ተከታዮቹ እርስ በርስ መዋደድ፣ አንድነታቸውን መጠበቅና ትእዛዛቱን መፈጸም እንደሚያስፈልጋቸው አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል። (ዮሐ. 15:10, 12, 13) ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጣቸው ምክር ምንኛ ጠቃሚ ነው! ይህ ምክር በዚያን ጊዜ ጠቃሚ እንደነበር ሁሉ ዛሬም ጠቃሚ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ