-
ዛሬ ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1999 | መስከረም 15
-
-
3, 4. (ሀ) በዛሬው ጊዜ ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው መሠረታዊ ነገር ምንድን ነው? (ለ) የኢየሱስን ፈለግ በቅርብ መከተል ያለብን ለምንድን ነው?
3 በኢየሱስ አገልግሎት መገባደጃ ዓመት ላይ ሐዋርያቱ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ወደ አንድ ትልቅ ተራራ፣ ምናልባትም ወደ አርሞንዔም ተራራ ተረተር ሳይሆን አይቀርም፣ አብረውት ሄዱ። በዚያም ኢየሱስ ዕጹብ ድንቅ ክብር ተጎናጽፎ የሚያሳይ ትንቢታዊ ራእይ የተመለከቱ ሲሆን አምላክ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” ብሎ ሲናገር ሰምተዋል። (ማቴዎስ 17:1-5) በመሠረቱ ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ነገር ልጁን እንድንሰማ እንዲሁም ምሳሌውንና ትምህርቱን እንድንከተል ነው። (ማቴዎስ 16:24) በመሆኑም ሐዋርያው ጴጥሮስ “ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና” ሲል ጽፏል።—1 ጴጥሮስ 2:21
-
-
ዛሬ ይሖዋ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1999 | መስከረም 15
-
-
5. ክርስቲያኖች በየትኛው ሕግ ሥር ናቸው? ይህስ ሕግ ተግባራዊ መሆን የጀመረው መቼ ነው?
5 ኢየሱስን መስማትና እሱን መምሰል ምን ማድረግን ይጠይቃል? በአንድ ሕግ ሥር መሆን ማለት ነውን? ጳውሎስ “እኔ ራሴ ከሕግ በታች [አይደለሁም]” ሲል ጽፏል። እዚህ ላይ እየተናገረ ያለው ስለ “አሮጌው ቃል ኪዳን” ማለትም ከእስራኤላውያን ጋር ስለተደረገው የሕግ ቃል ኪዳን ነበር። ጳውሎስ “በክርስቶስ ሕግ በታች” መሆኑን ግን አምኗል። (1 ቆሮንቶስ 9:20, 21፤ 2 ቆሮንቶስ 3:14) አሮጌው የሕግ ቃል ኪዳን ሲያበቃ በዛሬው ጊዜ የሚገኙ የይሖዋ አገልጋዮች ሁሉ ሊታዘዙት የሚገባውን “የክርስቶስን ሕግ” የያዘ “አዲስ ኪዳን” ተተካ።—ሉቃስ 22:20፤ ገላትያ 6:2፤ ዕብራውያን 8:7-13
-