የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአምላክን ትንቢታዊ ቃል በትኩረት ተከታተል
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 1
    • 6. (ሀ) ኢየሱስ ተአምራዊ ለውጡን ራእይ ብሎ የጠራው ለምንድን ነው? (ለ) መለወጡ የምን ነገር ነጸብራቅ ነበር?

      6 ይህ ዕጹብ ድንቅ ክንውን የተፈጸመው ኢየሱስና ሦስቱ ሐዋርያት ሌሊቱን ባሳለፉበት ከሔርሞን ተራራ ሸንተረሮች በአንዱ ላይ ሳይሆን አይቀርም። የኢየሱስ ተአምራዊ ለውጥ የታየው ሌሊት እንደነበረ አያጠራጥርም። ይህም ይበልጥ አንጸባራቂና አስደናቂ እንዲሆን አድርጎታል። ኢየሱስ ይህን ምልክት ራእይ ብሎ የጠራበት አንዱ ምክንያት ከሞቱ ብዙ ጊዜ ሆኗቸው የነበሩት ሙሴና ኤልያስ በዚያ ቦታ የተገኙት ቃል በቃል ባለመሆኑ ነው። በዚያ ቦታ በእውን ተገኝቶ የነበረው ክርስቶስ ብቻ ነው። (ማቴዎስ 17:​8, 9 NW ) ኢየሱስ እንዲህ ባለ አንጸባራቂ ሁኔታ መለወጡ ጴጥሮስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ኢየሱስ በንጉሣዊ ሥልጣኑ በሚገኝበት ጊዜ የሚኖረውን ግርማ በጥቂቱ እንዲመለከቱ አስችሏቸዋል። ሙሴና ኤልያስ የኢየሱስን ቅቡዓን ተባባሪ የመንግሥት ወራሾች የሚያመለክቱ ሲሆን ራእዩ ኢየሱስ ስለ መንግሥቱና ስለ ወደፊት ንግሥናው የሰጠውን ምሥክርነት አጠናክሮታል።

  • የአምላክን ትንቢታዊ ቃል በትኩረት ተከታተል
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ሚያዝያ 1
    • 8. (ሀ) አምላክ ስለ ልጁ የተናገረው ነገር በምን ላይ ያተኮረ ነበር? (ለ) ኢየሱስ በተአምር በተለወጠ ጊዜ የታየው ደመና ምን ያመለክታል?

      8 በጣም አስፈላጊ የነበረው “በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው” የሚለው አምላክ የተናገረው ነገር ነበር። ይህ መግለጫ ፍጥረት ሙሉ በሙሉ ሊታዘዝለት የሚገባው አምላክ የሾመው ንጉሥ ኢየሱስ መሆኑን ያረጋግጣል። በዚህ ጊዜ የጋረዳቸው ዳመና የዚህ ትንቢታዊ ራእይ ፍጻሜ በዓይን የማይታይ መሆኑን የሚያመለክት ነበር። ኢየሱስ በንጉሣዊ ሥልጣኑ በማይታይ ሁኔታ የመገኘቱን ‘ምልክት’ በሚገነዘቡ ሰዎች የማስተዋል ዓይን ብቻ የሚስተዋል ይሆናል። (ማቴዎስ 24:​3) እንዲያውም ኢየሱስ የሰው ልጅ ከሙታን ከመነሣቱ በፊት ራእዩን ለማንም እንዳይናገሩ ሐዋርያቱን ማስጠንቀቁ የሚከብረውና ግርማ የሚቀዳጀው ሞቶ ከተነሣ በኋላ እንደሆነ ያመለክታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ