የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የጉባኤውን ሰላምና ንጽሕና መጠበቅ
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 14 ኢየሱስ በክርስቲያኖች መካከል የሚፈጠሩ ከባድ ችግሮች እንዴት መፈታት እንዳለባቸው ገልጿል። በቅደም ተከተል የዘረዘራቸውን እርምጃዎች ተመልከት፦ “ወንድምህ ቢበድልህ [1] አንተና እሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ጥፋቱን በግልጽ ንገረው። ከሰማህ ወንድምህን ታተርፋለህ። የማይሰማህ ከሆነ ግን [2] ማንኛውም ጉዳይ ሁለት ወይም ሦስት ምሥክሮች በሚሰጡት የምሥክርነት ቃል ስለሚጸና አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ ሂድ። እነሱንም ካልሰማ [3] ለጉባኤ ተናገር። ጉባኤውንም እንኳ የማይሰማ ከሆነ እንደ አሕዛብና እንደ ቀረጥ ሰብሳቢ አድርገህ ቁጠረው።”—ማቴ. 18:15-17

  • የጉባኤውን ሰላምና ንጽሕና መጠበቅ
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 18 “አንተና እሱ ብቻችሁን ሆናችሁ” ጥፋቱን በመንገር ወንድምህን ማትረፍ ካልቻልክ ኢየሱስ እንዳለው ‘አንድ ወይም ሁለት ሰው ይዘህ በመሄድ’ ወንድምህን እንደገና ልታነጋግረው ትችላለህ። የምትወስዳቸው ሰዎችም ዓላማቸው ወንድምህን ማትረፍ እንድትችል መርዳት መሆን ይኖርበታል። ተፈጽሟል ለተባለው ድርጊት የዓይን ምሥክር የሆኑ ሰዎችን ብትወስድ ይመረጣል፤ የዓይን ምሥክሮች ከሌሉ ግን ውይይታችሁን የሚከታተሉ አንድ ወይም ሁለት ምሥክሮች ይዘህ መሄድ ትችላለህ። በተለይ ደግሞ እነዚህ ሰዎች መፍትሔ የሚያሻውን ጉዳይ በተመለከተ ልምድ ያላቸው ከሆኑ በእርግጥ በደል ተፈጽሟል አልተፈጸመም የሚለውን መለየት ይችሉ ይሆናል። ምሥክር እንዲሆኑ የተመረጡት ሰዎች ሽማግሌዎች ከሆኑ ጉባኤውን እንደሚወክሉ ተደርገው መታየት የለባቸውም፤ ምክንያቱም ይህን እንዲያደርጉ የወከላቸው የሽማግሌዎች አካል አይደለም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ