-
ወንድምህን ገንዘብ ልታደርገው ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥቅምት 15
-
-
የጎለመሰ ሰው እርዳታ ማግኘት
12, 13. (ሀ) ኢየሱስ በጠቀሰው መሠረት ስህተትን ለማስተካከል በሁለተኛ ደረጃ የሚወሰደው እርምጃ ምንድን ነው? (ለ) ይህን እርምጃ በሥራ ላይ ለማዋል ምን ተገቢ የሆነ ምክር ተሰጥቷል?
12 አንተ ከበድ ያለ ስህተት ብትፈጽምና ሌሎች አንተን ለመርዳት በሚያደርጉት ጥረት በአንዴ ተስፋ ቆርጠው ቢተዉህ ደስ ይልሃል? ደስ እንደማይልህ የታወቀ ነው። በተመሳሳይም ወንድምህን ገንዘብ ለማድረግና ከአንተና ከሌሎች ጋር አምላክን ተቀባይነት ባለው መንገድ ማምለክ ይችል ዘንድ ለመርዳት በመጀመሪያው እርምጃ ብቻ ጥረትህን ማቆም እንደሌለብህ ኢየሱስ አመልክቷል። ኢየሱስ መወሰድ ያለበትን ሁለተኛ እርምጃ እንዲህ በማለት አስቀምጦታል:- “ባይሰማህ ግን፣ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፣ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ።”
13 ኢየሱስ “አንድ ወይም ሁለት” ሰው ይዘህ ሂድ ብሏል። ኢየሱስ የመጀመሪያውን እርምጃ ከወሰድክ በኋላ ችግሩን ለሌሎች ሰዎች ለማውራት፣ ለተጓዥ የበላይ ተመልካች ለመንገር ወይም ለሌሎች በደብዳቤ ለማሳወቅ ነፃ ትሆናለህ አላለም። አንተ ስህተት እንደተሠራ ብታምንም ጉዳዩ ገና ሙሉ በሙሉ አልተረጋገጠም። የተሳሳተ ወሬ በማውራት በኋላ እንደ ስም አጥፊ መቆጠር እንደማትፈልግ ግልጽ ነው። (ምሳሌ 16:28፤ 18:8) ሆኖም ኢየሱስ አንድ ወይም ሁለት ሰዎችን ይዘህ መሄድ እንደምትችል ተናግሯል። ለምን? እነዚህስ ሰዎች እነማን ሊሆኑ ይችላሉ?
14. ሁለተኛውን እርምጃ በምንወስድበት ወቅት እነማንን ይዘን ልንሄድ እንችላለን?
14 ወንድምህ ኃጢአት መፈጸሙን እንዲያምንና ከአንተም ሆነ ከአምላክ ጋር ያለውን ሰላም ጠብቆ ማቆየት ይችል ዘንድ ንስሐ እንዲገባ በመቀስቀስ ወንድምህን ገንዘብ ለማድረግ እየጣርክ ነው። ይህንንም ዳር ማድረስ ይቻል ዘንድ ከአንተ ጋር የሚሄዱት “አንድ ወይም ሁለት” ሰዎች ስህተቱ ሲፈጸም የተመለከቱ ቢሆኑ ይመረጣል። ምናልባት ችግሩ ሲደርስ በአካል የነበሩ ወይም በንግድ ጉዳይ ምን ነገር እንደተፈጸመ (ወይም ምን ነገር ሳይደረግ እንደቀረ) በቂ መረጃ ያላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። እንደነዚህ ያሉ ምሥክሮችን ማግኘት የማይቻል ከሆነ እንዲህ ዓይነት ችግሮችን በመፍታት ረገድ ጥሩ ተሞክሮ ያላቸውና የተፈጸመው ነገር በትክክል ስህተት መሆን አለመሆኑን በሚገባ መለየት የሚችሉ ሰዎች ሊሆኑ ይገባል። ከዚህም በላይ በሌላ ወቅት መገኘት የሚያስፈልጋቸው ቢሆን እንኳ የተባለውን ነገር በትክክል አስታውሰው መመሥከር የሚችሉ፣ የቀረቡትን እውነታዎችና የተደረጉትን ጥረቶች በእርግጠኝነት መናገር የሚችሉ መሆን አለባቸው። (ዘኁልቁ 35:30፤ ዘዳግም 17:6) ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ከሁለቱም ወገን ያልሆኑ ገለልተኛ ሰዎች ወይም ዳኞች አይደሉም፤ ከዚያ ይልቅ እዚያ የተገኙበት ምክንያት የአንተንም ሆነ የእነርሱን ወንድም ገንዘብ ለማድረግ ነው።
15. ሁለተኛውን እርምጃ የምንወስድ ከሆነ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጠቃሚ እርዳታ ሊሰጡ የሚችሉት ለምንድን ነው?
15 የምትወስዳቸው ሰዎች የግድ የጉባኤ ሽማግሌዎች መሆን አለባቸው ብለህ ማሰብ የለብህም። ሆኖም ሽማግሌዎች መንፈሳዊ ብቃት ያላቸው የጎለመሱ ሰዎች በመሆናቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ። እነዚህ ሽማግሌዎች “ከነፋስ እንደ መሸሸጊያ ከዐውሎ ነፋስም እንደ መጠጊያ፣ በጥም ቦታም እንደ ወንዝ ፈሳሽ፣ በበረሀም አገር እንደ ትልቅ ድንጋይ ጥላ ይሆና[ሉ]።” (ኢሳይያስ 32:1, 2) ወንድሞችንና እህቶችን በምክንያታዊነት በማወያየትና በማስተካከል ረገድ ተሞክሮ አላቸው። እንዲሁም ስህተት የፈጸመው ግለሰብ ‘ስጦታ በሆኑት በእነዚህ ወንዶች’ ላይ ትምክህቱን ለመጣል አይቸገርም።c (ኤፌሶን 4:8, 11, 12) እነዚህ የጎለመሱ ሰዎች በተገኙበት ጉዳዩን በግልጥ መነጋገርና ከእነርሱ ጋር በጸሎት መካፈል ጉዳዩን በአዲስ መልክ ለማየትና ፈጽሞ መፍትሔ የሌለው የመሰለውን ጉዳይ መቋጫ እንዲገኝለት ለማድረግ ይችላል።—ከያዕቆብ 5:14, 15 ጋር አወዳድር።
-
-
ወንድምህን ገንዘብ ልታደርገው ትችላለህመጠበቂያ ግንብ—1999 | ጥቅምት 15
-
-
c አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንዲህ በማለት ሐሳብ ሰጥተዋል:- “አንዳንድ ጊዜ ስህተት የፈጸመ አንድ ግለሰብ አንድ ሰው በተለይ ደግሞ ከእርሱ የተለየ አመለካከት ያለው ሰው ከሚሰጠው ምክር ይልቅ ሁለት ወይም ሦስት (በተለይ በሌሎች ዘንድ አክብሮትን ያተረፉ) ሰዎች የሚሰጡትን ምክር ለመቀበል ይበልጥ ፈቃደኛ ሆኖ ይገኛል።”
-