የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አለመግባባትን የምትፈቱት እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ሐምሌ 15
    • “ወንድምህም ቢበድልህ፣ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፣ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው ባይሰማህ ግን፣ በሁለት ወይም በሦስት ምስክር አፍ ነገር ሁሉ እንዲጸና፣ ዳግመኛ አንድ ወይም ሁለት ከአንተ ጋር ውሰድ፤ እነርሱንም ባይሰማ፣ ለቤተ ክርስቲያን ንገራት፤ ደግሞም ቤተ ክርስቲያንን ባይሰማት፣ እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ።—ማቴዎስ 18:15–17

  • አለመግባባትን የምትፈቱት እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1994 | ሐምሌ 15
    • ችግሩ ሊፈታ ካልቻለ ለጉባኤ ይቀርባል። በመጀመሪያ ይህ የሚያመለክተው የአይሁድ ሽማግሌዎችን ነበር፤ በኋላ ግን የክርስቲያን ጉባኤ ሽማግሌዎችን የሚያመለክት ሆነ። ንስሐ የማይገባው ኃጢአተኛ ከጉባኤው መወገድ ሊያስፈልገው ይችላል። አይሁዳውያን ይርቋቸው እንደነበሩት ግለሰቦች ማለትም “እንደ አረመኔና እንደ ቀራጭ ይሁንልህ” ማለት ትርጉሙ ይህ ነበር። ይህ ከባድ እርምጃ እንዲሁ በማንኛውም ክርስቲያን በግለሰብ ደረጃ ሊወሰድ አይችልም። እንዲህ ዓይነቱን እርምጃ የመውሰድ ሥልጣን ያላቸው ጉባኤውን የሚወክሉ የተሾሙ ሽማግሌዎች ብቻ ናቸው።—ከ1 ቆሮንቶስ 5:13 ጋር አወዳድር።

      ንስሐ የማይገባ ኃጢአተኛ ሊወገድ የሚችል መሆኑ ማቴዎስ 18:15–17 ቀላል ስለሆነ አለመግባባት እንደማይናገር ያሳያል። ኢየሱስ ከባድ በደሎችን ማመልከቱ ነበር፤ ሆኖም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ግለሰቦች ብቻ ሊፈቱት የሚችሉት ዓይነት ነው። ለምሳሌ ያህል በደሉ የተበደለውን ሰው ስም የሚያጠፋ ሐሜት ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ቀጥሎ ያሉት ጥቅሶች ኢየሱስ ከፍተኛ ዕዳ ስለተሰረዘለት ጨካኝ ባሪያ ምሳሌ መናገሩን ስለሚገልጹ ጉዳዩ ገንዘብ ነክ ነገሮችን የሚመለከት ይሆናል። (ማቴዎስ 18:23–35) በተባለው ጊዜ ያልተከፈለ ብድር በሁለቱ ግለሰቦች መካከል በቀላሉ ሊፈታ የሚችል ጊዜያዊ ችግር ብቻ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የተበደረው ሰው ዕዳውን አልከፍልም ብሎ ድርቅ ካለ ከባድ ኃጢአት ይኸውም ሌብነት ይሆናል።

      በሁለት ክርስቲያኖች ብቻ ሊፈቱ የማይችሉ ሌሎች ኃጢአቶች አሉ። በሙሴ ሕግ መሠረት ከባድ ኃጢአቶች መነገር ነበረባቸው። (ዘሌዋውያን 5:1፤ ምሳሌ 29:24) ልክ እንደዚሁም የጉባኤውን ንጽሕና የሚነኩ ከባድ ኃጢአቶች ለክርስቲያን ሽማግሌዎች መነገር አለባቸው።

      ይሁን እንጂ በአብዛኛው በክርስቲያኖች መካከል የሚፈጠረው ግጭት ለዚህ የሚያደርስ አይደለም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ