የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስለ ወይን እርሻ የተነገሩ ሁለት ምሳሌዎች
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ በመቀጠል ሌላም ምሳሌ ተናገረ። በዚህ ምሳሌ ላይ የሃይማኖት መሪዎቹ ጥፋት አምላክን አለማገልገላቸው ብቻ እንዳልሆነ አመልክቷል። እነዚህ ሰዎች ክፉ ናቸው። ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “አንድ ሰው የወይን እርሻ አለማ፤ ዙሪያውንም አጠረው፤ ጉድጓድ ቆፍሮም የወይን መጭመቂያ አዘጋጀ፤ ማማም ሠራለት፤ ከዚያም ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ። ወቅቱ ሲደርስ ከወይኑ ፍሬ ድርሻውን ከገበሬዎቹ እንዲያመጣለት አንድ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ። እነሱ ግን ይዘው ደበደቡት፤ ባዶ እጁንም ሰደዱት። በድጋሚ ሌላ ባሪያ ወደ እነሱ ላከ፤ እሱንም ራሱን ፈነከቱት፤ ደግሞም አዋረዱት። ሌላም ባሪያ ላከ፤ እሱን ደግሞ ገደሉት፤ ሌሎች ብዙዎችንም ላከ፤ አንዳንዶቹን ደበደቡ፤ አንዳንዶቹን ደግሞ ገደሉ።”—ማርቆስ 12:1-5

      ኢየሱስን የሚያዳምጡት ሰዎች ምሳሌውን ይረዱ ይሆን? ኢሳይያስ የተናገረውን የሚከተለውን ውግዘት አዘል ሐሳብ ያስታውሱ ይሆናል፦ “የሠራዊት ጌታ የይሖዋ የወይን እርሻ የእስራኤል ቤት ነውና፤ የይሁዳ ሰዎች እሱ ይወደው የነበረው የአትክልት ቦታ ናቸው። ፍትሕን ሲጠብቅ እነሆ፣ ግፍ ይፈጸማል።” (ኢሳይያስ 5:7) የኢየሱስ ምሳሌም ከዚህ ጋር ይመሳሰላል። ባለ ርስቱ ይሖዋ ሲሆን የወይን እርሻው ደግሞ የአምላክ ሕግ እንደ አጥር ከለላ የሆነለት የእስራኤል ብሔር ነው። ይሖዋ፣ ሕዝቡን ለማስተማርና መልካም ፍሬ እንዲያፈሩ ለመርዳት ነቢያት ልኳል።

  • ስለ ወይን እርሻ የተነገሩ ሁለት ምሳሌዎች
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ይህን ሲናገሩ ሳያውቁት የፈረዱት በራሳቸው ላይ ነው፤ ምክንያቱም የይሖዋ “የወይን እርሻ” የሆነውን የእስራኤልን ብሔር ከሚያስተዳድሩት “ገበሬዎች” መካከል እነሱም ይገኙበታል። ይሖዋ ከእነዚህ ገበሬዎች ከሚጠብቃቸው ፍሬዎች አንዱ፣ በልጁ ማለትም በመሲሑ ማመን ሲሆን ይህን መጠበቁም ተገቢ ነው። ኢየሱስ የሃይማኖት መሪዎቹን ትኩር ብሎ በመመልከት እንዲህ አለ፦ “እንዲህ የሚለውን የቅዱሳን መጻሕፍት ቃል አላነበባችሁም? ‘ግንበኞች የናቁት ድንጋይ፣ የማዕዘን ራስ ድንጋይ ሆነ። ይህ የይሖዋ ሥራ ነው፤ ለዓይናችንም ድንቅ ነው።’” (ማርቆስ 12:10, 11) ከዚያም ኢየሱስ “የአምላክ መንግሥት ከእናንተ ተወስዶ ፍሬውን ለሚያፈራ ሕዝብ ይሰጣል የምላችሁ ለዚህ ነው” በማለት ነጥቡን ግልጽ አደረገ።—ማቴዎስ 21:43

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ