-
ምሥራቹ እየተሰበከ ያለው እንዴት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ሁሉም ሰዎች ምሥራቹ እንዲደርሳቸው ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን
የይሖዋ ምሥክሮች በሁሉም ቦታ ለሚኖሩ ሰዎች ምሥራቹን ለመስበክ ልዩ ጥረት ያደርጋሉ። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
የይሖዋ ምሥክሮች ምሥራቹን ለመስበክ ከሚያደርጉት ጥረት ጋር በተያያዘ አንተን የሚያስገርምህ ምንድን ነው?
ማቴዎስ 22:39ን እና ሮም 10:13-15ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
የስብከቱ ሥራችን ሰዎችን እንደምንወድ የሚያሳየው እንዴት ነው?
ይሖዋ ምሥራቹን ለሚሰብኩ ሰዎች ምን አመለካከት አለው?—ሮም 10:15ን ተመልከት።
-
-
በአምላክ ፊት ንጹሕ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ሱሶችን አስወግድ
ይሖዋ ማንኛውንም መጥፎ ልማድ እንድናሸንፍ ይረዳናል
ሲጋራ የምታጨስ ወይም ዕፆችን አላግባብ የምትጠቀም ከሆነ እነዚህን ሱሶች ማሸነፍ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመረዳት አትቸገርም። ታዲያ በዚህ ረገድ ምን ሊረዳህ ይችላል? እነዚህ ሱሶች በሕይወትህ ላይ የሚያሳድሩትን ተጽዕኖ ለማሰብ ሞክር። ማቴዎስ 22:37-39ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አንድ ሰው ሲጋራ ማጨሱ ወይም ዕፆችን አላግባብ መጠቀሙ ከይሖዋ ጋር ያለውን ዝምድና የሚነካበት እንዴት ነው?
እንዲህ ማድረጉ በቤተሰቡና በዙሪያው ባሉ ሰዎችስ ላይ ምን ተጽዕኖ ያሳድራል?
ሱስ ካለብህ፣ ይህን ሱስ ለማስወገድ ዕቅድ አውጣ።b ቪዲዮውን ተመልከቱ።
ፊልጵስዩስ 4:13ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
አንድ ሰው የመጸለይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን የማጥናትና በስብሰባዎች ላይ የመገኘት ጥሩ ልማድ ማዳበሩ መጥፎ ልማዶችን ለማሸነፍ ኃይል የሚሰጠው እንዴት ነው?
5. ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችንና ልማዶችን ለማስወገድ ትግል አድርግ
ቆላስይስ 3:5ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
የብልግና ምስሎችን መመልከት፣ ሴክስቲንግc እንዲሁም ማስተርቤሽን በይሖዋ ዓይን ርኩስ እንደሆኑ ማወቅ የምንችለው እንዴት ነው?
ይሖዋ በሥነ ምግባር ንጹሕ እንድንሆን መጠበቁ ምክንያታዊ ይመስልሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?
መጥፎ ሐሳቦችን ማስወገድ የሚቻለው እንዴት ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ።
ኢየሱስ ሥነ ምግባራዊ ንጽሕናችንን ለመጠበቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን የሚያሳይ ምሳሌ ተናግሯል። ማቴዎስ 5:29, 30ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ኢየሱስ ቃል በቃል በሰውነታችን ላይ ጉዳት ማድረስ እንዳለብን መናገሩ አልነበረም፤ ከዚህ ይልቅ ቆራጥ እርምጃ መውሰድ እንዳለብን ማመልከቱ ነበር። አንድ ሰው ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ ምን ዓይነት ቆራጥ እርምጃ ሊወስድ ይችላል?d
ንጹሕ ያልሆኑ ሐሳቦችን ለማስወገድ እየታገልክ ከሆነ ይሖዋ የምታደርገውን ጥረት ከፍ አድርጎ ይመለከታል። መዝሙር 103:13, 14ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ እየታገልክ ከሆነ ይህ ጥቅስ ተስፋ እንዳትቆርጥ የሚረዳህ እንዴት ነው?
ተስፋ አትቁረጥ!
አንድ መጥፎ ልማድ ሲያገረሽብህ ‘ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም፤ ታዲያ ምን አታገለኝ?’ ብለህ ልታስብ ትችላለህ። ሆኖም ይህን ለማሰብ ሞክር፦ አንድ ሯጭ ተደናቅፎ ወደቀ ማለት በውድድሩ ተሸነፈ ማለት አይደለም፤ ደግሞም ሩጫውን ከመነሻው መጀመር አያስፈልገውም። በተመሳሳይም አንድ መጥፎ ልማድ አገረሸብህ ማለት በምታደርገው ትግል ተሸነፍክ ማለት አይደለም፤ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ያደረግከው ጥረትም ከንቱ ይሆናል ማለት አይደለም። አንድን መጥፎ ልማድ ለማሸነፍ በምታደርገው ትግል እንዲህ ያለ ነገር ማጋጠሙ የሚጠበቅ ነው። ስለዚህ ተስፋ አትቁረጥ! በይሖዋ እርዳታ ያለብህን መጥፎ ልማድ ማሸነፍ ትችላለህ።
-