የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ከክፉ ትውልድ’ መዳን
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ኅዳር 1
    • 11. (ሀ) በመሠረቱ ሂ ጄኒያ ሃውቴ የተባለው ቃል አጠቃቀም ምን እንደሆነ ለማወቅ የምንመራው በየትኛው ባለ ሥልጣን ነው? (ለ) ይህ ባለ ሥልጣን ይህን ቃል የተጠቀመበት እንዴት ነው?

      11 በመሠረቱ ይህን ጉዳይ የሚመረምሩ ክርስቲያኖች አስተሳሰባቸውን የሚመሩት በመንፈስ አነሣሽነት የጻፉት የወንጌል ጸሐፊዎች የኢየሱስን ቃላት ለመዘገብ ሂ ጄኒያ ሃውቴ ወይም “ይህ ትውልድ” የሚሉትን የግሪክኛ ቃላት እንዴት እንደተጠቀመባቸው በማጤን ነው። ቃሉ በተደጋጋሚ ጊዜያት አሉታዊ በሆነ መንገድ ተሠርቶበታል። ይህም በመሆኑ የአይሁድ ሃይማኖታዊ መሪዎችን “እባቦች፣ የእፉኝት ልጆች” ካላቸው በኋላ “በዚህ ትውልድ” ላይ የገሃነም ፍርድ እንደሚበየን ተናግሯል። (ማቴዎስ 23:33, 36) ይሁን እንጂ ይህ ፍርድ የሚበየነው በግብዞቹ ቀሳውስት ላይ ብቻ ነበርን? ፈጽሞ አልነበረም። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ኢየሱስ በተደጋጋሚ ጊዜያት “ይህ ትውልድ” የሚሉትን ቃላት ሰፋ ባለ መንገድ በአንድ ዓይነት ሁኔታ ሲጠቀምባቸው ሰምተዋል። ይህ ሁኔታ ምን ነበር?

  • ‘ከክፉ ትውልድ’ መዳን
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | ኅዳር 1
    • 13. ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ በተገኙበት ‘ይህ ክፉ ትውልድ’ በማለት የጠራቸውና ያወገዛቸው እነማንን ነው?

      13 በ31 እዘአ መገባደጃ ላይ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ በገሊላ የሚያደርጉትን ሁለተኛ የስብከት ዘመቻቸውን ሲጀምሩ “ከጻፎችና ከፈሪሳውያን አንዳንዶቹ” ኢየሱስን ምልክት እንዲያሳያቸው ጠየቁት። ኢየሱስ ለእነሱና በዚያ ለነበሩት ‘ሕዝብ’ እንዲህ አላቸው፦ “ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል፣ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም። ዮናስ በዓሣ አንባሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል።. . . ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።” (ማቴዎስ 12:38–46) በግልጽ ለመረዳት እንደሚቻለው “ይህ ክፉ ትውልድ” የሃይማኖት መሪዎችን እና በኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ አማካኝነት የተፈጸመውን ምልክት በፍጹም ያላስተዋለውን ‘ሕዝብ’ ያቀፈ ነው።d

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ