የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አንተ ራስህ ሲፈጸም ያየኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
    • 25 ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ከፍተኛ ስጋት የፈጠሩ ሌሎች አራዊት እንዳሉ ይጠቁመናል። ነቢዩ ሕዝቅኤል ዓመፀኛ የሆኑ ሰዎችን ከአራዊት ጋር በማወዳደር እንደሚከተለው ብሏል:- “በውስጥዋ ያሉ አለቆችዋ የስስትን ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሱ ዘንድ ነፍሶችንም ያጠፉ ዘንድ እንደሚናጠቁ ተኩላዎች ናቸው።” (ሕዝቅኤል 22:​27) ኢየሱስ ‘የዓመፃ ብዛት’ እንደሚኖር ትንቢት ሲናገር እርሱ በሥልጣኑ በሚገኝበት ወቅት እንደነዚህ ያሉ ‘አራዊት’ በምድር ላይ እንደሚኖሩ መግለጹ ነበር ለማለት ይቻላል። (ማቴዎስ 24:​12) የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ጳውሎስም “በመጨረሻው ቀን” ሰዎች “ገንዘብን የሚወዱ . . . ራሳቸውን የማይገዙ፣ ጨካኞች መልካም የሆነውን የማይወዱ” እንደሚሆኑ ተናግሯል። (2 ጢሞቴዎስ 3:​1-3) ከ1914 ወዲህ ይህ ነገር ተከስቷልን?

      26-28. እንደ “አራዊት” ያሉ ወንጀለኞች በምድር ላይ እያደቡ መሆናቸውን የሚያሳዩት ከዓለም ዙሪያ የተገኙት ሪፖርቶች የትኞቹ ናቸው?

      26 በትክክል ተከስቷል። በዓለም ዙሪያ ካሉት ትላልቅ ከተሞች በአንዱ የምትኖር ከሆነ ይህ ለአንተ አዲስ አይደለም። ይሁን እንጂ የምትጠራጠር ከሆነ በቅርቡ በጋዜጦች ላይ ከወጡ ዘገባዎች የተወሰዱትን ሐሳቦች ተመልከት። ከኮሎምቢያ:- “ባለፈው ዓመት ፖሊስ . . . 10,000 የሚያክሉ ነፍስ ግድያዎችንና 25,000 የሚያክሉ በመሣሪያ የተፈጸሙ የዝርፊያ ወንጀሎችን መዝግቧል።” ከቪክቶሪያ፣ አውስትራሊያ:- “የከባድ ወንጀሎች መጠን በእጅጉ ጨምሯል።” ከዩናይትድ ስቴትስ:- “በኒው ዮርክ የሚፈጸመው ግድያ እስካሁን ታይቶ ወደማይታወቅ ከፍተኛ ደረጃ እያሻቀበ ነው።” “ባለፈው ዓመት ዴትሮይት በመላው የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት ካሉት ትላልቅ ከተሞች መካከል ከነዋሪው ቁጥር አንጻር ከፍተኛውን የነፍስ ግድያ ቁጥር በመያዝ የቀዳሚነቱን ስፍራ ከጌሪ ተረክባለች። ከ100,000 ነዋሪዎች መካከል 58 የሚሆኑት ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።”

      27 ከዚምባቡዌ:- “የሕፃናትን ሕይወት የማጥፋት ወንጀል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።” ከብራዚል:- “እዚህ የሚፈጸመው ወንጀልም ሆነ መሣሪያው በገፍ ስለሆነ ዓመፅ እንደተፈጸመ መስማት የሚያስገርም ዜና መሆኑ ቀርቷል።” ከኒው ዚላንድ:- “የፆታ ጥቃቶችና ሌሎች ከባድ ወንጀሎች ፖሊስን በእጅጉ እያሳሰቡ መጥተዋል።” “በኒው ዚላንድ ውስጥ አንዱ በሌላው ላይ የሚፈጽመው የወንጀል ዓይነት እጅግ አረመኔያዊ እየሆነ መጥቷል።” ከስፔይን:- “ስፔይን እየጨመረ ከመጣው ወንጀል ጋር ትንቅንቅ ይዛለች።” ከኢጣሊያ:- “የሲሲሊያ ወንበዴዎች ከገጠማቸው ሽንፈት ዳግም አንሰራርተው የግድያ ዘመቻ እያካሄዱ ነው።”

  • አንተ ራስህ ሲፈጸም ያየኸው የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
    • 29, 30. በኢየሱስ ትንቢት ፍጻሜ መሠረት በሕዝበ ክርስትና ውስጥ ያለው ሃይማኖታዊ ሁኔታ ምን ይመስላል?

      29 ኢየሱስ በሥልጣኑ በሚገኝበት ወቅት በሚኖረው በችግር የታመሰ ጊዜ ውስጥ ሃይማኖትስ ምን ያደርግ ይሆን? በአንድ በኩል ኢየሱስ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ እንደሚጨምር ትንቢት ተናግሯል:- “ብዙ ሐሰተኞች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ።” (ማቴዎስ 24:​11) በሌላ በኩል ደግሞ በጥቅሉ ሲታይ በሕዝበ ክርስትና ውስጥ ሰዎች ለአምላክ እምብዛም ደንታ የሌላቸው እንደሚሆኑ ተናግሯል። “የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።”​—⁠ማቴዎስ 24:​12

      30 ይህ ዛሬ በሕዝበ ክርስትና ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ነገር ጥሩ አድርጎ የሚገልጽ ነው። በአንድ በኩልም ዋና ዋናዎቹ አብያተ ክርስቲያናት ድጋፍ እያጡ መጥተዋል። በአንድ ወቅት ጠንካራ የፕሮቴስታንቶች ይዞታ በነበረው በሰሜን አውሮፓና በእንግሊዝ ሃይማኖት የተረሳ ነገር ሆኗል። በተመሳሳይም የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በካህናት እጥረት እንዲሁም የደጋፊዎቿ ቁጥር በመመናመኑ ችግር ላይ ወድቃለች። በሌላ በኩል ደግሞ ትናንሽ ሃይማኖታዊ ወገኖች በፍጥነት እየተበራከቱ ነው። ከምሥራቃውያን ሃይማኖቶች የሚወጡ ኑፋቄዎች እንደ አሸን ፈልተዋል። ስስታም የቴሌቪዥን ወንጌላውያንም በሚልዮን የሚቆጠር ዶላር ያጋብሳሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ