-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
‘ከዚያ በኋላ’ መጨረሻው ይመጣል
10. ቶት የተባለውን የግሪክኛ ቃል የምናተኩርበት ለምንድን ነው? ትርጉሙስ ምንድን ነው?
10 ኢየሱስ የአንዳንድ ሁኔታዎችን የአፈጻጸም ቅደም ተከተል ተናግሯል። እንዲህ አለ፦ “ይህ የመንግሥት ወንጌል . . . ይሰበካል፣ በዚያን ጊዜም መጨረሻው ይመጣል።” የእንግሊዝኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “በዚያን ጊዜ” በሚለው ቃል ቦታ የገባውን “ዜን” የተባለ ቃል አብዛኛውን ጊዜ “ስለዚህ” ወይም “ነገር ግን” የሚል ትርጉም በሚሰጥ መንገድ ይጠቀሙበታል። (ማርቆስ 4:15, 17፤ 13:23) ይሁን እንጂ ከላይ በተጠቀሰው በማቴዎስ 24:14 ላይ የገባው “ዜን” የሚለው ቃል ቶት ከተባለው የግሪክኛ ተውሳከ ግሥ የተገኘ ነው።c የግሪክኛ ቋንቋ ሊቃውንት ቶት “በቀጣይነት የሚፈጸምን አንድ ነገር” ወይም “በጊዜ ረገድ ቀጥሎ የሚፈጸምን ሁኔታ” ለማስተዋወቅ የሚያገለግል “የጊዜ አመልካች ተውሳከ ግሥ” እንደሆነ ይናገራሉ። ስለዚህ ኢየሱስ መንግሥቱ እንደሚሰበክና በዚያን ጊዜ (‘ከዚያ በኋላ’ ወይም ‘ቀጥሎ’) “መጨረሻው” እንደሚመጣ ተንብዮአል። ይህ “መጨረሻ” የትኛው ነው?
-
-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
c ቶት የተባለው ቃል በማቴዎስ መጽሐፍ ውስጥ 80 ጊዜ (9 ጊዜ በምዕራፍ 24 ውስጥ) በሉቃስ መጽሐፍ ውስጥ ደግሞ 15 ጊዜ ተጠቅሶ ይገኛል። ማርቆስ ቶት የተባለውን ቃል የተጠቀመበት ስድስት ጊዜ ብቻ ሲሆን አራቱ የተጠቀሱት ‘በምልክቱ’ ውስጥ ነው።
-