-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
13. ክርስቲያኖች ኢየሱስ እንዲሸሹ የሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ሰምተው እንዲሸሹ ያስቻላቸው ምን ነበር?
13 ይሁን እንጂ ሮማውያኑ ከኢየሩሳሌም አካባቢ ከተመለሱ ከከተማይቱ መሸሽ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የኢየሱስ ቃላት የተፈጸመው ነገር ‘የኢየሩሳሌም ጥፋት መቅረቡን’ እንደሚያመለክት በግልጽ ስለሚያሳዩ ነው። (ሉቃስ 21:20) አዎን፣ ጥፋት መቅረቡን ያመለክት ነበር። ኢየሱስ “ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ እንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ” ይደርሳል በማለት ተንብዮ ነበር። ከሦስት ዓመት ተኩል በኋላ ማለትም በ70 እዘአ በጄኔራል ቲቶ ይመራ የነበረው የሮም ሠራዊት በኢየሩሳሌም ላይ ታላቅ መከራ አደረሰ። (ማቴዎስ 24:21፤ ማርቆስ 13:19) ይሁን እንጂ ኢየሱስ ይህን ጥፋት ከዚያ በፊትም ሆነ ከዚያ በኋላ ከደረሱት መከራዎች የሚበልጥ መከራ እንደሆነ የገለጸው ለምን ነበር?
14. በ70 እዘአ በኢየሩሳሌም ላይ የደረሰው ጥፋት ከዚያም በፊት ሆነ ከዚያ በኋላ ያልደረሰ “ታላቅ መከራ” ነው ለማለት የምንችለው ለምንድን ነው?
14 ባቢሎናውያን በ607 ከዘአበ ኢየሩሳሌምን ባድማ አድርገዋት ነበር። በዚህ መቶ ዘመናችንም ይህች ከተማ አስከፊ ጦርነቶችም ተፈጽመውባታል። ያም ሆኖ ግን በ70 እዘአ የተፈጸመው በዓይነቱ ልዩ የሆነ ታላቅ መከራ ነበር። ለአምስት ወራት ያህል በቆየው ዘመቻ በቲቶ ይመራ የነበረው የሮማውያን ሠራዊት አይሁዳውያንን ድል አድርጎ 1,100,000 ሰዎችን ሲገድል 100,000 የሚያክሉ ሰዎችን ባሪያ አድርጎ ወስዷል። ከዚህም በላይ ሮማውያን ኢየሩሳሌምን ጨርሰው አፈራረሷት። ይህም በፊት ተቀባይነት የነበረው በቤተ መቅደሳቸው ማዕከልነት ይፈጸም የነበረው ተቀባይነት ያለው የአይሁዳውያን የአምልኮ ሥርዓት ለዘለቄታው እንዳበቃለት ያረጋግጣል። (ዕብራውያን 1:2) አዎን፣ በ70 እዘአ የተፈጸመው ነገር “ከዓለም መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ [በዚያ ከተማ፣ ሕዝብና ሥርዓት ላይ ደርሶ የማያውቅ] ከእንግዲህም ከቶ የማይሆን ታላቅ መከራ” ተደርጎ ቢቆጠር ትክክል ነው።—ማቴዎስ 24:21d
-
-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
d ማቲው ሄንሪ የተባሉት እንግሊዛዊ ደራሲ እንዲህ ብለዋል፦ “ከለዳውያን በኢየሩሳሌም ላይ ያደረሱት ጥፋት በጣም አስከፊ ቢሆንም ይኸኛው ይበልጥ የከፋ ነበር። የአይሁዳውያንን ዘር . . . ፈጽሞ ለማጥፋት የቃጣ ነበር።”
-
-
የመገኘትህ ምልክት ምን ይሆናል?’መጠበቂያ ግንብ—1994 | የካቲት 15
-
-
በ70 እዘአ የደረሰው መከራ በኢየሩሳሌምም ሆነ በአይሁዳውያን ሥርዓት ላይ ከደረሱት መከራዎች ሁሉ የሚበልጥ ነበር
-