የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው?”
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
    • 16. ስለ ኢየሱስ መምጣት የሚናገሩት ሌሎቹ ጥቅሶች የትኞቹ ናቸው?

      16 ኢየሱስ ታማኝና ልባም ባሪያን አስመልክቶ ሲናገር “ጌታው ተመልሶ በሚመጣበት ጊዜ እንዲህ ሲያደርግ ካገኘው ያ ባሪያ ደስተኛ ነው!” ብሏል። ስለ ደናግሎቹ በተናገረው ምሳሌ ላይ ኢየሱስ “[ደናግሎቹ ዘይት] ሊገዙ ሄደው ሳሉም ሙሽራው ደረሰ [“መጣ፣” አዲሱ መደበኛ ትርጉም]” ብሏል። ስለ ታላንት በተናገረው ምሳሌ ላይ “ከረጅም ጊዜ በኋላ የእነዚያ ባሪያዎች ጌታ [መጣ]” በማለት ተናግሯል። በዚያው ምሳሌ ላይ ጌታው “እኔም ተመልሼ ስመጣ ገንዘቡን ከነወለዱ እወስደው ነበር” ብሏል። (ማቴ. 24:46፤ 25:10, 19, 27) ስለ ኢየሱስ መምጣት የሚናገሩት እነዚህ ጥቅሶች የሚያመለክቱት የትኛውን ጊዜ ነው?

      17. በ⁠ማቴዎስ 24:46 ላይ የተጠቀሰውን የኢየሱስ መምጣት አስመልክቶ በጽሑፎቻችን ላይ ምን ተገልጾ ነበር?

      17 መጨረሻ ላይ የተጠቀሱት ስለ ኢየሱስ መምጣት የሚናገሩት አራቱ ጥቅሶች ኢየሱስ በ1918 መምጣቱን የሚያመለክቱ እንደሆነ ቀደም ሲል በጽሑፎቻችን ላይ ተገልጾ ነበር። ስለ “ታማኝና ልባም ባሪያ” የሚናገረውን ጥቅስ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። (ማቴዎስ 24:45-47⁠ን አንብብ።) በቁጥር 46 ላይ የተገለጸው የኢየሱስ መምጣት፣ ኢየሱስ በ1918 የቅቡዓኑን መንፈሳዊ ሁኔታ ለመመርመር የመጣበትን ጊዜ እንደሚያመለክትና ባሪያው በጌታው ንብረት ላይ የተሾመው በ1919 እንደሆነ እናምን ነበር። (ሚል. 3:1) ይሁንና የኢየሱስን ትንቢት በጥልቀት ስንመረምር የትንቢቱ አንዳንድ ገጽታዎች የሚፈጸሙበትን ጊዜ በተመለከተ ያለን መረዳት መስተካከል እንዳለበት እንገነዘባለን። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

      18. የኢየሱስን ትንቢት ሙሉ ሐሳብ ስንመለከት፣ ኢየሱስ የሚመጣበትን ጊዜ በተመለከተ ምን መደምደሚያ ላይ እንድንደርስ ያደርገናል?

      18 ከ⁠ማቴዎስ 24:46 በፊት ባሉት ጥቅሶች ውስጥ የሚገኘው ‘መምጣት’ የሚለው ቃል በሁሉም ቦታዎች ላይ የሚያመለክተው ኢየሱስ በታላቁ መከራ ወቅት ፍርድ ለመስጠትና ለማስፈጸም የሚመጣበትን ጊዜ ነው። (ማቴ. 24:30, 42, 44) በተጨማሪም አንቀጽ 12 ላይ እንደተመለከትነው በ⁠ማቴዎስ 25:31 ላይ የተጠቀሰው የኢየሱስ መምጣት የሚያመለክተው ይህንኑ ጊዜ ማለትም ኢየሱስ ለፍርድ የሚመጣበትን ጊዜ ነው። በመሆኑም በ⁠ማቴዎስ 24:46, 47 ላይ በተጠቀሰው መሠረት ኢየሱስ ታማኙን ባሪያ በንብረቱ ሁሉ ላይ ለመሾም የሚመጣውም ወደፊት ነው ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ነው። በእርግጥም ኢየሱስ የተናገረውን ትንቢት ሙሉ ሐሳብ ስንመለከት፣ ስለ ኢየሱስ መምጣት የሚናገሩት ከላይ ያየናቸው ስምንቱም ጥቅሶች የሚያመለክቱት እሱ በታላቁ መከራ ወቅት ለፍርድ የሚመጣበትን ጊዜ እንደሆነ ግልጽ ያደርግልናል።

  • “ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚፈጸሙት መቼ ነው?”
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ሐምሌ 15
    • e አንቀጽ 15፦ ‘መምጣት’ እና ‘መድረስ’ የሚሉት ቃላት የተተረጎሙት ኤርኮማይ ከሚለው የግሪክኛ ግስ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ