የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ንቁ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ደናግሉ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ፣ ከመገኘቱና ከሥርዓቱ መደምደሚያ ምልክት ጋር በተያያዘ ሐዋርያቱ ላቀረቡለት ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ቆይቷል። አሁንም ተጨማሪ ምሳሌ በመጠቀም ጥበብ ያዘለ ምክር ሰጣቸው። የምልክቱን ፍጻሜ ኢየሱስ በሥልጣኑ በሚገኝበት ጊዜ በሕይወት የሚኖሩ ሰዎች ይመለከቱታል።

      ኢየሱስ ምሳሌውን ሲጀምር እንዲህ አለ፦ “መንግሥተ ሰማያት መብራታቸውን ይዘው ሙሽራውን ሊቀበሉ ከወጡ አሥር ደናግል ጋር ሊመሳሰል ይችላል። አምስቱ ሞኞች፣ አምስቱ ደግሞ ልባሞች ነበሩ።”—ማቴዎስ 25:1, 2

      ኢየሱስ፣ መንግሥተ ሰማያትን ከሚወርሱት ደቀ መዛሙርቱ ግማሾቹ ሞኞች ግማሾቹ ደግሞ ልባሞች እንደሆኑ እየተናገረ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ከመንግሥተ ሰማያት ጋር በተያያዘ እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር ንቁ መሆኑ አሊያም ትኩረቱ መከፋፈሉ በራሱ ምርጫ ላይ የተመካ መሆኑን እየገለጸ ነው። ሆኖም ኢየሱስ፣ እያንዳንዱ የእሱ አገልጋይ ታማኝነቱን መጠበቅና የአባቱን በረከት ማግኘት እንደሚችል እርግጠኛ ነው።

      በምሳሌው ላይ አሥሩም ደናግል ሙሽራውን ለመቀበልና ሠርጉን ለማጀብ ወጥተዋል። ሙሽራው ሲደርስ ደናግሉ መብራታቸውን አብርተው አካባቢውን ያደምቃሉ፤ ሙሽራው ሙሽራይቱን ወደተዘጋጀላት ቤት ሲያመጣት መብራታቸውን ማብራታቸው ለእሱ ያላቸውን አክብሮት ያሳያል። ታዲያ በምሳሌው ላይ የተገለጹት ደናግል ምን አጋጠማቸው?

  • ንቁ ስለ መሆን የተሰጠ ትምህርት—ደናግሉ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ሐዋርያቱ በምሳሌው ላይ የተጠቀሰው ሙሽራ ኢየሱስን እንደሚያመለክት መረዳት ይችላሉ። ከዚህ ቀደም ኢየሱስ ራሱን ከሙሽራ ጋር አመሳስሏል። (ሉቃስ 5:34, 35) ልባሞቹ ደናግልስ ማንን ያመለክታሉ? ኢየሱስ፣ መንግሥት ስለሚወርሰው “ትንሽ መንጋ” ሲናገር “ወገባችሁን ታጠቁ፤ መብራታችሁንም አብሩ” ብሎ ነበር። (ሉቃስ 12:32, 35) በመሆኑም ስለ ደናግሉ በሚገልጸው በዚህ ምሳሌ ላይ ኢየሱስ እንደ እነሱ ስላሉ ታማኝ ደቀ መዛሙርት እየተናገረ እንደሆነ ሐዋርያቱ መገንዘብ ይችላሉ። ታዲያ ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ተጠቅሞ ማስተላለፍ የፈለገው መልእክት ምንድን ነው?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ