የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ነቅታችሁ ትጠብቃላችሁ?’
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
    • 9. (ሀ) ኢየሱስ ከእንቅልፍ ጋር በተያያዘ ምን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል? (ለ) ቅቡዓኑ ‘ሙሽራው እየመጣ ነው!’ ለሚለው ጥሪ ምን ምላሽ ሰጥተዋል? (የግርጌ ማስታወሻውንም ተመልከት።)

      9 እነዚህ ደናግል ተሰናድተው እንዲጠብቁ የረዳቸው ሌላው ነገር ደግሞ ንቁ መሆናቸው ነው። ለመሆኑ በሌሊት ለረጅም ሰዓት ሲጠብቁ እንቅልፍ የሚጫጫናቸው አንዳንድ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ሊኖሩ ይችላሉ? አዎን። ኢየሱስ፣ ስለ አሥሩ ደናግል ሲናገር ሙሽራው የዘገየ በመሰላቸው ወቅት “ሁሉም እንቅልፍ ተጫጫናቸውና ተኙ” ብሏል። ኢየሱስ፣ ፈቃደኛና ዝግጁ የሆኑ ሰዎችም እንኳ ሥጋ ደካማ መሆኑ ሊያስቸግራቸው እንደሚችል ጠንቅቆ ያውቃል። ታማኝ የሆኑ ቅቡዓን በምሳሌው ላይ የተሰጠውን ይህንን ማስጠንቀቂያ ተግባራዊ በማድረግ ምንጊዜም ንቁ ለመሆን ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ጥረት እያደረጉ ነው። በምሳሌው ላይ እንደተገለጸው ‘ሙሽራው እየመጣ ነው!’ የሚል ጥሪ በሌሊት ሲሰማ ሁሉም ደናግል ተነስተዋል። እስከ መጨረሻው የጸኑት ግን ንቁዎቹ ብቻ ናቸው። (ማቴ. 25:5, 6፤ 26:41) በዛሬው ጊዜ ስላሉት ታማኝ ቅቡዓንስ ምን ማለት ይቻላል? በመጨረሻዎቹ ቀናት ያሉት ታማኝ ቅቡዓንም ‘ሙሽራው እየመጣ ነው!’ ለሚለው ጥሪ ምላሽ ሰጥተዋል። ኢየሱስ ሊመጣ መሆኑን የሚጠቁመውን ጠንካራ ማስረጃ በማመን እሱ የሚመጣበትን ጊዜ ተሰናድተው እየተጠባበቁ ጸንተው ቆይተዋል።a ይሁንና የምሳሌው መደምደሚያ የሚያተኩረው በአንድ የተወሰነ ጊዜ ላይ ነው። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

  • ‘ነቅታችሁ ትጠብቃላችሁ?’
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
    • a ከምሳሌው ማየት እንደሚቻለው ‘ሙሽራው እየመጣ ነው!’ (ቁጥር 6) የሚለው ጥሪ በተሰማበትና ሙሽራው በመጣበት ወይም በደረሰበት ወቅት (ቁጥር 10) መካከል ግልጽ የሆነ የጊዜ ልዩነት አለ። ንቁ የሆኑት ቅቡዓን የኢየሱስን መገኘት የሚጠቁመውን ምልክት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሁሉ አስተውለዋል። በመሆኑም ኢየሱስ ‘እንደመጣ’ ይኸውም ንጉሣዊ ሥልጣን ይዞ እየገዛ እንደሆነ ተገንዝበዋል። ያም ቢሆን ኢየሱስ እስኪመጣ ወይም እስኪደርስ ድረስ መጽናት አለባቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ