የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ስለ “ነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” የተገኘው የእውቀት ብርሃን
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 13. ልባሞቹ ቆነጃጅት ሰነፎቹ ላቀረቡላቸው ልመና መልስ የሰጡት እንዴት ነው?

      13 ከቆነጃጅቱ ክፍል የሆኑት ሰነፎችስ ምን ሆኑ? ኢየሱስ በመቀጠል እንዲህ አለ:- “ሰነፎቹም ልባሞቹን:- መብራታችን ሊጠፋብን ነው፤ ከዘይታችሁ ስጡን አሉአቸው። ልባሞቹ ግን መልሰው ምናልባት ለእኛና ለእናንተ ባይበቃስ፤ ይልቅስ ወደሚሸጡት ሄዳችሁ ለራሳችሁ ግዙ አሉአቸው።”— ማቴዎስ 25:8, 9

  • ስለ “ነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ” የተገኘው የእውቀት ብርሃን
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 15. (ሀ) የሰላሙ ጊዜ ሲጀምር ከቆነጃጅቱ መካከል የመንፈሳዊ ስንፍና ዝንባሌዎችን ማሳየት የጀመሩት እነማን ነበሩ? (ለ) ልባሞቹ ቆነጃጅት በመንፈሳዊ ሰነፍ የሆኑትን ቆነጃጅት ለመርዳት ያልቻሉት ለምንድን ነው?

      15 የሰላሙ ወቅት በሚጀምርበት ጊዜ ራሳችንን ወስነን ተጠምቀናል ይሉ ከነበሩት ተባባሪዎች ውስጥ አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ስንፍና ማሳየት ጀመሩ። ከመጀመሪያው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር ፕሬዝዳንት ከቻርልስ ቴዝ ራስል ሞት በኋላ በአዲሱ የማኅበሩ ፕሬዝዳንት በጄ. ኤፍ. ራዘርፎርድ ከሚመራው የይሖዋ አምላክ የሚታይ መሣሪያ ጋር በመሆን አዲስ ወደተፈጠሩት ሁኔታዎች መንፈስ ሳይገቡ ቀሩ። በእርግጥም ልባቸው ነገሮች እየተከናወኑ ካሉበት መንገድ ጋር የተስማማ አልነበረም። ይሖዋ ከሕዝቡ ጋር ግንኙነት ለሚያደርግበት መንገድ አድናቆት እንደጎደላቸው አሳዩ። በዚህ ምክንያት ልባሞቹን ቆነጃጅት የሚመስሉት ደቀ መዛሙርት ራሳቸውን የበለጠ እያገለሉ በሄዱት በእነዚህ ሰነፎች ልብ ውስጥ ልባዊ የሆነ እውነተኛ የትብብር መንፈስ ለማስገባት አልቻሉም።

      16. የሰነፎቹ ቆነጃጅት መንፈሳዊ ስንፍና ገሃድ መውጣት የጀመረው እንዴት ነበር?

      16 በዚህ መንገድ መንፈሳዊው ስንፍናቸው ገሃድ መውጣት ጀመረ። እንዴት? ሙሽራው መገኘቱን የሚያሳዩ አዲስ የተፈጠሩ ሁኔታዎች ወደፊት እየገፉ በሚሄዱበትና መንፈሳዊው ብርሃን በጣም አስፈላጊ በነበረበት በዚያ ታላቅ ወቅት ላይ ምሳሌያዊውን ዘይት ለመያዝ ባለመቻላቸው ነው። ስለዚህ በምሳሌያዊ አነጋገር እያንዳንዱ መብራቱን ቦግ አድርጎ በማብራት እርሱን ለመቀበል የሚወጣበት ጊዜ ነበር። ይሁን እንጂ መብራታቸው እየጠፋባቸው በሄዱት ሰነፍ ቆነጃጅት የተመሰሉት ከልባሞቹ ተለይተው ሄዱ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ