የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን አታውቁም’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 15
    • ‘ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን አታውቁም’

      “እንግዲህ ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ።”​—ማቴ. 25:13

  • ‘ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን አታውቁም’
    መጠበቂያ ግንብ—2012 | መስከረም 15
    • 1-3. (ሀ) ኢየሱስ የተናገራቸውን ሁለት ምሳሌዎች ጎላ አድርገው የሚገልጹት የትኞቹ ሁኔታዎች ናቸው? (ለ) ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ያስፈልገናል?

      አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን በጣም አንገብጋቢ የሆነ ቀጠሮ እንዳለውና ወደ ቀጠሮው ቦታ በመኪና እንድትወስደው እንደሚፈልግ ነገረህ እንበል። ሆኖም ባለሥልጣኑን ወደ ስብሰባው ቦታ ለመውሰድ ጥቂት ደቂቃ ሲቀርህ መኪናህ በቂ ነዳጅ እንደሌለው አወቅክ። በመሆኑም ነዳጅ ለመቅዳት በፍጥነት ሄድክ። በዚህ መሃል ባለሥልጣኑ ተዘጋጅቶ ወጣ። ዞር ዞር እያለ ቢመለከትም ሊያገኝህ አልቻለም። በጣም ስለቸኮለ ሌላ ሰው እንዲወስደው አደረገ። ልክ እንደተመለስክ ባለሥልጣኑን ሌላ ሰው እንደወሰደው አወቅክ። በዚህ ጊዜ ምን ይሰማሃል?

      2 አሁን ደግሞ አንተ ራስህ ባለሥልጣን እንደሆንክ አድርገህ አስብ፤ አንድ በጣም አስፈላጊ የሆነ ሥራ እንዲሠሩልህ ብቃት ያላቸውን ሦስት ሰዎች መረጥክ እንበል። ስለ ሥራው በደንብ ገለጻ ካደረክላቸው በኋላ ሦስቱም ሥራውን ለመሥራት ፈቃደኞች ሆኑ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስትመለስ ግን ኃላፊነታቸውን የተወጡት ሁለቱ ብቻ እንደሆኑ ተገነዘብክ። የሚገርመው ደግሞ ኃላፊነቱን ያልተወጣው ግለሰብ ሰበብ አስባብ መደርደር ጀመረ። በዚያ ላይ ሥራውን ለመሥራት ሙከራ እንኳ አላደረገም። ታዲያ ስለዚህ ሰው ምን ይሰማሃል?

      3 ኢየሱስ፣ በመጨረሻው ቀን አንዳንድ ቅቡዓን ክርስቲያኖች ታማኝና ልባም መሆናቸውን ሲያሳዩ ሌሎቹ እንዲህ የማያደርጉት ለምን እንደሆነ ለማስረዳት ከላይ ከቀረቡት ሁኔታዎች ጋር የሚመሳሰሉትን ስለ ደናግሎቹና ስለ ታላንቱ የሚናገሩትን ምሳሌዎች ተጠቅሟል።a (ማቴ. 25:1-30) ኢየሱስ ሊያስተላልፍ የፈለገውን ነጥብ ጎላ አድርጎ ሲገልጽ “እንግዲህ ቀኑንም ሆነ ሰዓቱን ስለማታውቁ ዘወትር ነቅታችሁ ጠብቁ” ብሏል፤ ኢየሱስ እዚህ ላይ የጠቀሰው ‘ቀንና ሰዓት’ የሚያመለክተው በሰይጣን ዓለም ላይ የአምላክን ፍርድ ለማስፈጸም የሚመጣበትን ጊዜ ነው። (ማቴ. 25:13) ይህ ምክር በዛሬው ጊዜ ለምንገኘው ክርስቲያኖችም ይጠቅማል። ታዲያ ኢየሱስ ማበረታቻ በሰጠን መሠረት ዘወትር ነቅተን መጠበቃችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? ለመዳን ዝግጁ ሆነው ሲጠብቁ የነበሩት እነማን ናቸው? በዛሬው ጊዜ ነቅተን ለመጠበቅ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ