የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በክርስቶስ ገንዘብ አጠቃቀም ላይ የተደረገ መተሳሰብ
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 1. ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ ችግሮች የሌሉበት መንግሥት የትኛው ነው? ከዚህስ መንግሥት ጋር ሒሳብ መተሳሰብ የሚኖርባቸው እነማን ናቸው?

      ከአንዱ መንግሥት በስተቀር የኢኮኖሚ ችግር የሌለበት ምንም መንግሥት የለም። አብዛኞቹ መንግሥታት ከፍተኛ የገንዘብ ዕዳ አለባቸው። ይህ ችግር የማይነካው መንግሥት በአሁኑ ጊዜ በስፋት የሚታወጀው “መንግሥተ ሰማያት” ነው። (ማቴዎስ 25:1) አሁንም ቢሆን ያንን መንግሥት የሚያገለግሉና የዚያ ሰማያዊ መንግሥት የወደፊት አባላት የሆኑ በምድር ላይ ይገኛሉ። በሰው ዘር ታሪክ ሁሉ በጣም አስቸጋሪ በሆነው በዚህ ጊዜ ውስጥ እነዚህ “የመንግሥተ ሰማያት” አገልጋዮች ሒሳብ እንዲያስረክቡ ተጠይቀዋል። በአደራ የተሰጣቸውን ውድ ሀብት እንዴት እንደተጠቀሙበት ከመንግሥቱ ጋር መተሳሰብ ይኖርባቸዋል።

      2. ‘በሰላሙ መስፍን’ የተነገረን አንድ ምሳሌ ለመመርመር ፍላጐት ሊያድርብን የሚገባው ለምንድን ነው?

      2 ይህንን ጉዳይ በምሳሌ ለማስረዳት ‘ከመንግሥተ ሰማያት’ ተወካዮች ውስጥ ቀዳሚውን ቦታ የያዘው ከረጅም ጊዜ በፊት አንድ ምሳሌ ተናግሮ ነበር። ዛሬ ይህን ጉዳይ ለመመርመር ፍላጐት ሊያድርብን ይገባል፤ ምክንያቱም ‘የሰላሙ መስፍን’ ሙሉ የመግዛት ሥልጣን በመያዝ በመንግሥቱ ላይ ‘መገኘቱን’ ስለሚገልጸው “ምልክት” በተናገረው ሰፊ ትንቢት ውስጥ ስለጨመረው ነው። (ማቴዎስ 24:3 አዓት) በዛሬው ጊዜ የትንቢቱን ፍጻሜ ተከትለው የመጡት ውጤቶች የወደፊት ሕልውናችንን ወይም ሕይወታችንን ስለሚነኩ መላቀቅ በማይቻል ሁኔታ ውስጥ ገብተናል። “የሰላሙ መስፍን” በጎልጎታ መሥዋዕት ሆኖ ከመሞቱ ከጥቂት ቀኖች በፊት ለሐዋርያቱ ምሳሌውን የተናገረው በሚከተለው መንገድ ነበር።

  • በክርስቶስ ገንዘብ አጠቃቀም ላይ የተደረገ መተሳሰብ
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 3. ጌታቸው ከመሄዱ በፊት መክሊቶችን የተቀበሉት ባሮች እርሱ ሄዶ በነበረበት ጊዜ እንዴት አድርገው ተጠቅመውባቸው ነበር?

      3 “ቀኒቱንና ሰዓቲቱን አታውቁምና እንግዲህ ንቁ። ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ፣ ለአንዱ አምስት መክሊትa ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ። አምስት መክሊትም የተቀበለው ሄዶ ነገደበት ሌላም አምስት አተረፈ፤ እንዲሁም ሁለት የተቀበለው ሌላ ሁለት አተረፈ። አንድ የተቀበለው ግን ሄዶ ምድርን ቆፈረና የጌታውን ገንዘብ ቀበረ።

  • በክርስቶስ ገንዘብ አጠቃቀም ላይ የተደረገ መተሳሰብ
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 6 “ስለዚህ መክሊቱን ውሰዱበት አስር መክሊትም ላለው ስጡት፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና ይበዛለትማል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል። የማይጠቅመውንም ባሪያ በውጭ ወዳለው ጨለማ አውጡት። በዚያ ልቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”— ማቴዎስ 25:13–30

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ