-
ደስተኛ ለመሆን በእርግጥ ምን ያስፈልጋል?መጠበቂያ ግንብ—2004 | መስከረም 1
-
-
ይሁን እንጂ፣ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ወይም የሚያዝኑ ሰዎች እንዴት ደስተኛ ይባላሉ ብለን እንጠይቅ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ስለ ዓለም ሁኔታዎች ትክክለኛ አመለካከት አላቸው። በዘመናችን ‘በሚሠራው ጸያፍ ተግባር ያዝናሉ እንዲሁም ያለቅሳሉ።’ (ሕዝቅኤል 9:4) ይህ በራሱ ደስተኛ እንደማያደርጋቸው የታወቀ ነው። ይሁን እንጂ፣ አምላክ በምድር ላይ ጽድቅን የማስፈንና በግፍ ለተደቆሱት ፍትሕን የማምጣት ዓላማ እንዳለው ሲማሩ ደስታቸው ወደር አይኖረውም።—ኢሳይያስ 11:4
-
-
ደስተኛ ለመሆን በእርግጥ ምን ያስፈልጋል?መጠበቂያ ግንብ—2004 | መስከረም 1
-
-
የሚያዝኑ፣ ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ እንዲሁም በመንፈሳዊ የሚጎድላቸው ነገር እንዳለ የሚታወቃቸው ሰዎች ከፈጣሪ ጋር ጥሩ ወዳጅነት መመሥረት አስፈላጊ መሆኑን ይገነዘባሉ። ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መመሥረት ደስታ እንደሚያስገኝ የታወቀ ነው፤ ከአምላክ ጋር ጥሩ ዝምድና መመሥረት ደግሞ ከዚያ የበለጠ ደስታ ያስገኛል። አዎን፣ መለኮታዊውን አመራር ለመቀበል ፈቃደኛ የሆኑ፣ ጽድቅን ከልብ የሚያፈቅሩ ሰዎች ደስተኞች መባላቸው የተገባ ነው።
-