-
ከታላንቱ ምሳሌ ትምህርት ማግኘትመጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
-
-
ክፉና ሰነፍ ባሪያ
14, 15. ኢየሱስ ከቅቡዓን ወንድሞቹ መካከል ብዙዎች ክፉና ሰነፍ እንደሚሆኑ መግለጹ ነበር? አብራራ።
14 በምሳሌው ላይ የተጠቀሰው የመጨረሻው ባሪያ በታላንቱ ከመነገድ፣ ሌላው ቀርቶ ታላንቱን ገንዘብ ለዋጮች ጋር ከማስቀመጥ ይልቅ መሬት ውስጥ ቀብሮታል። ይህ ባሪያ የጌታውን ጥቅም የሚነካ ነገር ሆን ብሎ በማድረጉ መጥፎ ዝንባሌ እንዳለው አሳይቷል። ጌታው “ክፉና ሰነፍ” ብሎ የጠራው መሆኑ የሚያስገርም አይደለም። ጌታው፣ የእሱን ታላንት ወስዶ አሥር ታላንት ላለው ባሪያ ሰጠው። ከዚያም ጌታው ክፉውን ባሪያ አስመልክቶ እንዲህ አለ፦ “ውጭ ወዳለው ጨለማ ጣሉት። በዚያም ያለቅሳል፣ በሐዘንም ጥርሱን ያፋጫል።”—ማቴ. 25:24-30፤ ሉቃስ 19:22, 23
15 ኢየሱስ ከጌታው ሦስት ባሪያዎች አንዱ ታላንቱን እንደቀበረው ሲገልጽ ከቅቡዓን ተከታዮቹ መካከል አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ክፉና ሰነፍ እንደሚሆኑ መጠቆሙ ነበር? በፍጹም። የምሳሌውን አውድ እንመልከት። ኢየሱስ ስለ ታማኝና ልባም ባሪያ በተናገረው ምሳሌ ላይ ባልንጀራዎቹ የሆኑትን ባሪያዎች ስለሚደበድብ ክፉ ባሪያ ጠቅሶ ነበር። ኢየሱስ ይህን ሲል ክፉ ባሪያ የሆነ ቡድን እንደሚኖር መናገሩ አልነበረም። ከዚህ ይልቅ ታማኙ ባሪያ፣ የክፉ ባሪያ ዓይነት ባሕርያት እንዳያንጸባርቅ ማሳሰቡ ነበር። በተመሳሳይም ኢየሱስ ስለ አሥሩ ደናግል በተናገረው ምሳሌ ላይ ከቅቡዓን ተከታዮቹ መካከል ግማሽ የሚሆኑት እንደ አምስቱ ሞኝ ደናግል እንደሚሆኑ መግለጹ አልነበረም። ከዚህ በተቃራኒ መንፈሳዊ ወንድሞቹ ንቁና ዝግጁ ካልሆኑ ምን ሊከሰት እንደሚችል ማስጠንቀቁ ነበር።f ከዚህ አንጻር፣ ኢየሱስ ስለ ታላንቱ የሚገልጸውን ምሳሌ ሲናገር በመጨረሻዎቹ ቀናት ከሚኖሩት ቅቡዓን ወንድሞቹ መካከል ብዙዎች ክፉና ሰነፍ እንደሚሆኑ እየገለጸ አልነበረም ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ይመስላል። ከዚህ ይልቅ ቅቡዓን ተከታዮቹ ምንጊዜም በትጋት እንዲሠሩ ማለትም በታላንታቸው ‘እንዲነግዱ’ እንዲሁም ክፉው ባሪያ ካሳየው ዝንባሌና ካደረገው ነገር እንዲርቁ እያስጠነቀቃቸው ነው።—ማቴ. 25:16
-