-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
7, 8. ኢየሱስ በጎቹን በተመለከተ ምን ብሏል? በመሆኑም እነሱን በተመለከተ ምን መደምደሚያ ላይ ልንደርስ እንችላለን?
7 በበጎች ላይ የሚሰጠውን ፍርድ በተመለከተ እንዲህ የሚል እናነባለን፦ “[ኢየሱስም] በቀኙ ያሉትን እንዲህ ይላቸዋል፦ እናንተ የአባቴ ብሩካን፣ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ። ተርቤ አብልታችሁኛልና፣ ተጠምቼ አጠጥታችሁኛልና፣ እንግዳ ሆኜ ተቀብላችሁኛልና፣ ታርዤ አልብሳችሁኛልና፣ ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፣ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። ጻድቃንም መልሰው ይሉታል፦ ጌታ ሆይ፣ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህ? እንግዳ ሆነህስ አይተን መቼ ተቀበልንህ? ወይስ ታርዘህ አይተን መቼ አለበስንህ? ወይስ ታመህ ወይስ ታስረህ አይተን መቼ ወደ አንተ መጣን? ንጉሡም መልሶ፦ እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል።”—ማቴዎስ 25:34–40
-
-
የበጎቹና የፍየሎቹ የወደፊት ዕጣ ምንድን ነው?መጠበቂያ ግንብ—1995 | ጥቅምት 15
-
-
10, 11. (ሀ) በጎቹ ለኢየሱስ ወንድሞች አንድ ዓይነት ደግነት ያደረጉ ሰዎችን በሙሉ ያካትታሉ ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ያልሆነው ለምንድን ነው? (ለ) በጎቹ እነማንን ያመለክታሉ?
10 ኢየሱስ ከወንድሞቹ ለአንዱ ትንሽ ቁራሽ ወይም አንድ ብርጭቆ ውኃ በመስጠት አነስተኛ ደግነት ያሳየ ሰው ሁሉ ከበጎቹ እንደ አንዱ ለመሆን ይበቃል ማለቱ ነበርን? እንዲህ ዓይነቱ የደግነት ተግባር ሰብዓዊ ደግነት ሊሆን እንደሚችል አሌ ባይባልም በዚህ ምሳሌ ላይ የተጠቀሱትን በጎች የሚመለከት ሌላ ነገር ያለ ይመስላል። ለምሳሌ ያህል ኢየሱስ ከወንድሞቹ ለአንዱ አንድ ዓይነት የደግነት ተግባር የፈጸሙ አምላክ የለም ባዮችን ወይም ቀሳውስትን መጥቀሱ እንዳልነበር የተረጋገጠ ነው። በሌላ በኩል ግን ኢየሱስ በጎቹን ሁለት ጊዜ “ጻድቃን” በማለት ጠርቷቸዋል። (ማቴዎስ 25:37, 46) ስለዚህ በጎቹ በአንድ የተወሰነ ጊዜ ውስጥ የክርስቶስ ወንድሞችን በትጋት የረዷቸውንና በአምላክ ፊት የጽድቅ አቋም ለማግኘት የሚያስፈልገውን እምነት ያሳዩ ሰዎችን ማመልከት ይኖርባቸዋል።
11 ለበርካታ መቶ ዘመናት እንደ አብርሃም የመሳሰሉ ብዙ ሰዎች በአምላክ ፊት የጽድቅ አቋም አግኝተዋል። (ያዕቆብ 2:21–23) ኖኅ፣ አብርሃምና ሌሎች ታማኝ ሰዎች በአምላክ መንግሥት ሥር በገነት ውስጥ የዘላለም ሕይወት ከሚወርሱት “ሌሎች በጎች” መካከል ናቸው። በቅርቡ ሌሎች በሚልዮን የሚቆጠሩ የሌሎች በጎች አባላት ከቅቡዓን ጋር “አንድ መንጋ” በመሆን እውነተኛውን አምልኮ ይዘዋል። (ዮሐንስ 10:16፤ ራእይ 7:9) እነዚህ ምድራዊ ተስፋ ያላቸው ሰዎች የክርስቶስ ወንድሞች የመንግሥቱ አምባሳደሮች እንደሆኑ ስለሚገነዘቡ በሰብዓዊም ይሁን በመንፈሳዊ መንገድ ይረዷቸዋል። ኢየሱስ ሌሎች በጎች በምድር ላይ ላሉት ወንድሞቹ የሚያደርጉትን ነገር ለእሱ እንዳደረጉለት አድርጎ ይቆጥረዋል። ከእነዚህ መካከል ኢየሱስ በአሕዛብ ላይ ለመፍረድ በሚመጣበት ወቅት በሕይወት የሚኖሩት በጎች እንደሆኑ ይፈረድላቸዋል።
12. በጎቹ ለኢየሱስ ደግነት ስለማድረጋቸው ጥያቄ ያቀረቡት ለምን ሊሆን ይችላል?
12 ታዲያ በአሁኑ ጊዜ ከቅቡዓን ጋር ሆነው ምሥራቹን የሚሰብኩትና እነሱን የሚረዷቸው ሌሎች በጎች ከሆኑ “ጌታ ሆይ፣ ተርበህ አይተን መቼ አበላንህስ? ወይስ ተጠምተህ አይተን መቼ አጠጣንህስ?” ብለው የሚጠይቁት ለምንድን ነው? (ማቴዎስ 25:37) ብዙ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ምሳሌ ነው። ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ አማካኝነት ለመንፈሳዊ ወንድሞቹ ያለውን ጥልቅ አሳቢነት፣ ለእነሱ እንደሚያዝንና የእነሱን መከራ እንደሚካፈል አሳይቷል። ኢየሱስ ከዚህ ቀደም ሲል “እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፣ እኔን የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል” ብሎ ነበር። (ማቴዎስ 10:40) ኢየሱስ በዚህ ምሳሌ ላይ ይህን መሠረታዊ ሥርዓት ተጠቅሞ አንድ ሰው ለወንድሞቹ የሚደረገው ነገር (ጥሩም ይሁን መጥፎ) ወደ ሰማይ እንደሚደርስ አሳይቷል፤ ነገሩ በሰማይ ለእሱ የተደረገለት ያህል ነው። በተጨማሪም ኢየሱስ እዚህ ላይ በሚፈረድላቸውም ሆነ በሚፈረድባቸው ሰዎች ላይ አምላክ የሚሰጠውን ፍርድ ተገቢና ፍትሐዊ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ በማስቀመጥ የይሖዋ የፍርድ መመዘኛ አጉልቷል። ፍየሎቹ ‘በዓይናችን ብናይህ ኖሮ እንረዳህ ነበር’ የሚል ሰበብ ማቅረብ አይችሉም።
-