የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
    • 4 “የሰው ልጅ” እንዲሁም “ንጉሡ” የተባለው ኢየሱስ እንደሆነ የ1881 የጽዮን መጠበቂያ ግንብ ገልጾ ነበር። ቀደም ባሉት ዓመታት የነበሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፣ “ወንድሞቼ” የሚለው አገላለጽ ከክርስቶስ ጋር የሚገዙትን ብቻ ሳይሆን የፍጽምና ደረጃ ላይ የሚደርሱ በምድር የሚኖሩ የሰው ልጆችን በሙሉ እንደሚያመለክት ይሰማቸው ነበር። በጎቹ ከፍየሎቹ የሚለዩትም በክርስቶስ የሺህ ዓመት ግዛት ወቅት እንደሆነ ያስቡ ነበር። ሰዎች፣ በግ ተብለው የሚመደቡት ደግሞ በአምላክ የፍቅር ሕግ መሠረት ስለኖሩ እንደሆነ ያምኑ ነበር።

      5. በ1920ዎቹ ዓመታት ግንዛቤያችን ይበልጥ ግልጽ የሆነው እንዴት ነው?

      5 በ1920ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ይሖዋ፣ ሕዝቡ ከዚህ ምሳሌ ጋር በተያያዘ ያላቸው ግንዛቤ ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን አድርጓል። የጥቅምት 15, 1923 መጠበቂያ ግንብ “የሰው ልጅ” የተባለው ኢየሱስ እንደሆነ በድጋሚ ገለጸ። ይሁንና የክርስቶስን ወንድሞች ማንነት ሲያብራራ እነዚህ ሰዎች ከእሱ ጋር በሰማይ የሚገዙትን ብቻ እንደሚያመለክቱ የሚያሳይ አሳማኝ ቅዱስ ጽሑፋዊ ማስረጃ አቀረበ፤ በጎቹ ደግሞ በክርስቶስ መንግሥት አገዛዝ ሥር በምድር ላይ ለመኖር ተስፋ የሚያደርጉ ሰዎችን ያመለክታሉ። በጎቹ ከፍየሎቹ የሚለዩበትን ጊዜ በተመለከተስ ምን ሐሳብ ወጥቶ ነበር? በሺህ ዓመቱ ግዛት ወቅት የክርስቶስ ወንድሞች በሰማይ ከእሱ ጋር በመግዛት ላይ ስለሚሆኑ በዚያ ወቅት በምድር ያሉ ሰዎች ሊረዷቸውም ሆነ ችላ ሊሏቸው እንደማይችሉ መጽሔቱ አብራርቶ ነበር። በመሆኑም በጎቹ ከፍየሎቹ መለየት ያለባቸው ከሺህ ዓመቱ ግዛት በፊት ነው። ሰዎች፣ በግ ተብለው እንዲፈረድላቸው መሠረት የሚሆነው ነገር ደግሞ ኢየሱስን እንደ ጌታቸው አድርገው መቀበላቸውና የተሻለ ሁኔታ የሚገኘው ከእሱ መንግሥት መሆኑን ማመናቸው እንደሆነ መጽሔቱ ገልጿል።

  • የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
    • 7. በአሁኑ ጊዜ ምን ግልጽ የሆነ ግንዛቤ አለን?

      7 በአሁኑ ጊዜ የበጎቹንና የፍየሎቹን ምሳሌ በተመለከተ ግልጽ የሆነ ግንዛቤ አለን። በምሳሌው ላይ ስለተገለጹት ሰዎችና ቡድኖች ማንነት እንመልከት፤ “የሰው ልጅ” ወይም ንጉሥ የተባለው ኢየሱስ ነው። ንጉሡ “ወንድሞቼ” ያላቸው ሰዎች ከክርስቶስ ጋር በሰማይ የሚገዙ በመንፈስ የተቀቡ ወንዶችና ሴቶች ናቸው። (ሮም 8:16, 17) “በጎቹ” እና “ፍየሎቹ” የተባሉት ደግሞ ከሕዝቦች ሁሉ የተውጣጡ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ አይደሉም። ፍርድ የሚሰጥበትን ጊዜ በተመለከተስ ምን ማለት ይቻላል? ይህ ፍርድ የሚካሄደው በቅርቡ ይኸውም በታላቁ መከራ መደምደሚያ አካባቢ ነው። በሰዎች ላይ በግ ወይም ፍየል የሚለውን ፍርድ ለማስተላለፍ መሠረት የሚሆነው ነገር ምንድን ነው? ይህ ፍርድ የሚሰጠው፣ ሰዎች በምድር ላይ ላሉት በመንፈስ የተቀቡ የክርስቶስ ወንድሞች ያደረጉትን ነገር መሠረት በማድረግ ነው። የዚህ ሥርዓት ፍጻሜ በጣም በቀረበበት በአሁኑ ወቅት ይሖዋ ይህ ምሳሌ እንዲሁም በ⁠ማቴዎስ ምዕራፍ 24 እና 25 ላይ የሚገኙት ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ምሳሌዎች ደረጃ በደረጃ ግልጽ እንዲሆኑልን በማድረጉ ምንኛ አመስጋኞች ነን!

  • የክርስቶስን ወንድሞች በታማኝነት መደገፍ
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መጋቢት 15
    • 9 በመጀመሪያ ደረጃ፣ ኢየሱስ እያስተማረ ያለው በምሳሌ ተጠቅሞ መሆኑን ማስተዋል ይኖርብናል። በመሆኑም ቃል በቃል በጎችን ከፍየሎች ስለ መለየት እየተናገረ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በተመሳሳይም በግ እንደሆነ የተፈረደለት እያንዳንዱ ሰው የክርስቶስን ወንድሞች ቃል በቃል ማብላት፣ ማልበስ፣ መንከባከብ ወይም በታሰሩበት ወቅት መጠየቅ እንዳለበት መግለጹ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በበጎች የተመሰሉት ሰዎች ለወንድሞቹ ስለሚኖራቸው አመለካከት መናገሩ ነው። በጎቹ “ጻድቃን” የተባሉት፣ ክርስቶስ በምድር ላይ የተቀቡ ወንድሞች እንዳሉት ስለተገነዘቡና በእነዚህ የመጨረሻ ቀናት ቅቡዓኑን በታማኝነት ስለደገፏቸው ነው።—ማቴ. 10:40-42፤ 25:40, 46፤ 2 ጢሞ. 3:1-5

      10. በጎቹ ለክርስቶስ ወንድሞች ደግነት ማሳየት የሚችሉት እንዴት ነው?

      10 በሁለተኛ ደረጃ፣ ኢየሱስ የተናገረውን ምሳሌ አውድ እንመልከት። በወቅቱ ኢየሱስ ስለ መገኘቱና ስለዚህ ሥርዓት መደምደሚያ ምልክት እየተናገረ ነበር። (ማቴ. 24:3) ኢየሱስ በንግግሩ መጀመሪያ አካባቢ፣ የዚህን ምልክት አስደናቂ ገጽታ ገልጾ ነበር፤ ይኸውም የመንግሥቱ ምሥራች ‘በመላው ምድር መሰበኩ’ ነው። (ማቴ. 24:14) ስለ በጎቹና ፍየሎቹ ከመናገሩ በፊት ደግሞ የታላንቱን ምሳሌ ገልጿል። ቀደም ባለው ርዕስ ላይ እንደተብራራው ኢየሱስ ይህን ምሳሌ የተናገረው፣ በመንፈስ ቅዱስ የተቀቡ ደቀ መዛሙርቱ ወይም ‘ወንድሞቹ’ በስብከቱ ሥራ በቅንዓት መካፈል እንዳለባቸው አበክሮ ለመግለጽ ነው። ይሁንና ኢየሱስ በመንግሥቱ በሚገኝበት ወቅት በምድር ላይ የሚቀሩት ጥቂት ቁጥር ያላቸው ቅቡዓን መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት “ለሕዝቦች ሁሉ” ምሥራቹን መስበክ ከባድ እንደሚሆንባቸው የታወቀ ነው። የበጎቹና የፍየሎቹ ምሳሌ ቅቡዓኑ እርዳታ እንደሚያገኙ ይጠቁማል። በመሆኑም በጎች እንደሆኑ የሚፈረድላቸው ሰዎች ለክርስቶስ ወንድሞች ደግነት ማሳየት ከሚችሉባቸው ዋነኛ መንገዶች አንዱ በስብከቱ ሥራ እነሱን መደገፍ ነው። ይሁንና ይህ ድጋፍ ምን ይጨምራል? የሚያስፈልጋቸውን ቁሳዊ ነገር ወይም ማበረታቻ መስጠት ብቻ ነው? ወይስ ሌላም የሚያስፈልግ ነገር አለ?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ