-
‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’መጠበቂያ ግንብ—2013 | ታኅሣሥ 15
-
-
9. አንዳንዶች፣ ኢየሱስ ስለተጠቀመበት ቂጣ ምን ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት አላቸው?
9 ክርስቲያን ነን የሚሉ አንዳንድ ሰዎች ‘ኢየሱስ “ይህ ሥጋዬ ነው” ስላለ ቂጣው ተአምራዊ በሆነ መንገድ ቃል በቃል ወደ ኢየሱስ ሥጋ ተለውጧል’ ብለው ያስባሉ። ይሁን እንጂ ይህ ሐሳብ ከእውነታው የራቀ ነው።a ኢየሱስ ይህን በተናገረበት ወቅት የኢየሱስ ሥጋም ሆነ እንዲበሉት የሰጣቸው ያልቦካው ቂጣ በታማኝ ሐዋርያቱ ፊት ነበሩ። ከዚህ በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው ኢየሱስ በሌሎች ጊዜያት ያደርግ እንደነበረው ሁሉ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ እየተናገረ ነበር።—ዮሐ. 2:19-21፤ 4:13, 14፤ 10:7፤ 15:1
10. በጌታ ራት ላይ የሚቀርበው ቂጣ ምን ይወክላል?
10 ሐዋርያቱ እንዲበሉት የተሰጣቸው ቂጣ የኢየሱስን አካል የሚወክል ነው። ይሁንና ይህ አካል የትኛው ነው? በአንድ ወቅት የአምላክ አገልጋዮች ቂጣው የሚወክለው “የክርስቶስን አካል” ይኸውም የቅቡዓንን ጉባኤ እንደሆነ ያስቡ ነበር፤ እንዲህ ያሰቡት ኢየሱስ ቂጣውን የቆራረሰው ቢሆንም ከአጥንቶቹ መካከል ግን አንዱም ስላልተሰበረ ነው። (ኤፌ. 4:12፤ ሮም 12:4, 5፤ 1 ቆሮ. 10:16, 17፤ 12:27) ከጊዜ በኋላ ግን ቅዱሳን መጻሕፍትን ሲመረምሩ ቂጣው፣ ለኢየሱስ የተዘጋጀለትን ሰብዓዊ አካል እንደሚያመለክት ተገነዘቡ። ኢየሱስ ተሰቅሎ እስከ መሞት ድረስ ‘በሥጋው መከራ ተቀብሏል።’ ከዚህ አንጻር በጌታ ራት ላይ የሚቀርበው ቂጣ ኢየሱስ ‘ኃጢአታችንን የተሸከመበትን’ ሰብዓዊ አካል ይወክላል።—1 ጴጥ. 2:21-24፤ 4:1፤ ዮሐ. 19:33-36፤ ዕብ. 10:5-7
-
-
‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’መጠበቂያ ግንብ—2013 | ታኅሣሥ 15
-
-
15, 16. የጌታ ራት በሚከበርበት ወቅት ቂጣው ምን ይደረጋል?
15 ንግግሩ ሊያበቃ ሲቃረብ ተናጋሪው፣ ኢየሱስ ለሐዋርያቱ በሰጠው መመሪያ መሠረት በዓሉን የምናከብርበት ሰዓት እንደደረሰ ይገልጻል። እርሾ ያልገባበት ቂጣና ቀዩ ወይን ጠጅ፣ ከተናጋሪው አጠገብ ባለ ጠረጴዛ ላይ ሊቀመጡ ይችላሉ። ተናጋሪው፣ ኢየሱስ በዓሉን ባቋቋመበት ወቅት ስለተናገረውና ስላደረገው ነገር በሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ ላይ ትኩረት እንድናደርግ ይጋብዛል። ለምሳሌ ያህል፣ የማቴዎስ ዘገባ እንዲህ ይላል፦ “ኢየሱስ ቂጣ አንስቶ ከባረከ በኋላ ቆረሰው፤ ከዚያም ለደቀ መዛሙርቱ በመስጠት ‘እንኩ፣ ብሉ። ይህ ሥጋዬ ማለት ነው’ አለ።” (ማቴ. 26:26) ኢየሱስ፣ እርሾ ያልገባበትን ቂጣ በግራና በቀኙ ላሉት ሐዋርያት ለማከፋፈል ሲል ቆራርሶታል። በተመሳሳይም ሚያዝያ 14 በሚከበረው በዓል ላይ እርሾ ያልገባበት የተቆራረሰ ቂጣ ሳህን ላይ ተቀምጦ ታያለህ።
-