የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ ወደ ሐና ከዚያም ወደ ቀያፋ ተወሰደ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • በዚህ ጊዜ አጠገቡ ከቆሙት የቤተ መቅደስ ጠባቂዎች አንዱ ኢየሱስን በጥፊ መታውና “ለካህናት አለቃው የምትመልሰው እንዲህ ነው?” ሲል አረመው። ኢየሱስ ግን ምንም ጥፋት እንዳልሠራ ስለሚያውቅ “የተሳሳተ ነገር ተናግሬ ከሆነ ስህተቴ ምን እንደሆነ ንገረኝ፤ የተናገርኩት ነገር ትክክል ከሆነ ግን ለምን ትመታኛለህ?” ሲል መለሰለት። (ዮሐንስ 18:22, 23) ከዚያም ሐና ኢየሱስን ወደ አማቹ ወደ ቀያፋ ላከው።

      በዚህ ወቅት መላው የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት ይኸውም ሊቀ ካህናቱና የሕዝቡ ሽማግሌዎች እንዲሁም ጸሐፍት ተሰብስበዋል። የተሰበሰቡት በቀያፋ ቤት ነው። በፋሲካ ሌሊት እንዲህ ዓይነት ችሎት ማካሄድ ሕጉን የሚጥስ ቢሆንም ይህ የክፋት ዓላማቸውን ከማከናወን አላገዳቸውም።

      እነዚህ ሰዎች ከአድልዎ ነፃ የሆነ ፍርድ እንደማይሰጡ ምንም ጥያቄ የለውም። ኢየሱስ አልዓዛርን ከሞት ባስነሳበት ጊዜ የሳንሄድሪን ሸንጎ አባላት ኢየሱስን ለመግደል ወስነዋል። (ዮሐንስ 11:47-53) ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ የሃይማኖት መሪዎቹ ኢየሱስን ለመያዝና ለመግደል ሴራ ጠንስሰዋል። (ማቴዎስ 26:3, 4) በእርግጥም ኢየሱስ ሞት የተፈረደበት ገና ችሎት ፊት ሳይቀርብ ነው!

  • ጴጥሮስ ኢየሱስን ካደው
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
    • ኢየሱስ በጌትሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲያዝ ሐዋርያቱ ስለፈሩ ጥለውት ሸሹ። ሁለቱ ግን መሸሻቸውን አቁመው ተመለሱ። እነዚህ ሐዋርያት “ጴጥሮስና አንድ ሌላ ደቀ መዝሙር” እንደሆኑ ዘገባው ይገልጻል፤ ይህ ደቀ መዝሙር ሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ ከሁኔታው መረዳት ይቻላል። (ዮሐንስ 18:15፤ 19:35፤ 21:24) ምናልባትም ኢየሱስ ወደ ሐና እየተወሰደ ሳለ ሳይደርሱበት አልቀሩም። ሐና፣ ኢየሱስን ወደ ሊቀ ካህናቱ ቀያፋ ሲልከው ጴጥሮስና ዮሐንስ በርቀት ተከተሉት። በአንድ በኩል ለራሳቸው ሕይወት በመፍራት በሌላ በኩል ደግሞ ጌታቸው ስለሚደርስበት ነገር በመጨነቅ ልባቸው ለሁለት የተከፈለ ይመስላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ