-
“ሂዱና . . . ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ጥር
-
-
1-2. አንድ መልአክ በኢየሱስ መቃብር አጠገብ ያገኛቸውን ሴቶች ምን አላቸው? ኢየሱስ ራሱስ ምን የሚል መመሪያ ሰጣቸው?
ዕለቱ ኒሳን 16, 33 ዓ.ም. ነው። ፈሪሃ አምላክ ያላቸው የተወሰኑ ሴቶች ጎህ ሲቀድ ተነስተው፣ ከ36 ሰዓታት በፊት የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አስከሬን ወዳረፈበት የመቃብር ቦታ አመሩ። አስከሬኑን ጥሩ መዓዛ ባላቸው ቅመሞችና ዘይቶች ለመቀባት ተዘጋጅተው የሄዱት እነዚህ ሐዘን የደቆሳቸው ሴቶች መቃብሩ ጋ ሲደርሱ የሚያስገርም ነገር ገጠማቸው፤ መቃብሩ ባዶ ነበር! አንድ መልአክ ኢየሱስ ከሞት እንደተነሳ ለሴቶቹ ከነገራቸው በኋላ “ቀድሟችሁ ወደ ገሊላ ይሄዳል። እዚያም ታዩታላችሁ” አላቸው።—ማቴ. 28:1-7፤ ሉቃስ 23:56፤ 24:10
-
-
“ሂዱና . . . ሰዎችን ደቀ መዛሙርት አድርጉ”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ጥር
-
-
4 ኢየሱስ ሁሉም ተከታዮቹ እንዲሰብኩ ይፈልጋል። ትእዛዙን የሰጠው ለ11 ታማኝ ሐዋርያቱ ብቻ አይደለም። ይህን እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የማድረጉን ትእዛዝ በገሊላ በሚገኘው ተራራ ላይ በሰጠበት ወቅት በቦታው የነበሩት ሐዋርያት ብቻ ናቸው? መልአኩ ለሴቶቹ “እዚያም [በገሊላ] ታዩታላችሁ” እንዳላቸው እናስታውስ። ስለዚህ በስብሰባው ላይ ታማኝ ሴቶችም ተገኝተው መሆን አለበት። ይሁንና ሌሎች ሰዎችም ሳይገኙ አይቀሩም። ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ኢየሱስ “በአንድ ጊዜ ከ500 ለሚበልጡ ወንድሞች” እንደተገለጠ ተናግሯል። (1 ቆሮ. 15:6) ይህ የሆነው የት ነው?
-